ጥቂት ጥያቄ፣ እጅግ በጣም ብዙ ህዝብ፣ - TopicsExpress



          

ጥቂት ጥያቄ፣ እጅግ በጣም ብዙ ህዝብ፣ ትንሽ እንኳ የማይሰማ መንግስት! ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ዛሬም “ድምፃችን ይሰማ“ ሲሉ በአለም ዙሪያ አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡ በዛሬው ተቃውሞ፤ ከወትሮው በተለየ መልኩ፤ በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአንድ ላይ ተሰባስበው አቤት ሲሉ፣ እስከዛሬ የተቃውሞ ድምፃቸው ያልተሰማባቸው አካባቢዎችም ተቃውሞውን መቀላቀላቸው ተሰምቷል፡፡ ትዝ ይለናል… ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በመጀመሪያ የጠየቁት ሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎችን ብቻ ነበር፡፡ “መንግስት ሌላ የሃይማኖት አስተምሮ በግድ አይጫንብን እኛ እንደምን ማምለክ እንዳለብን እናውቃለን“ የሚለው… አንድ! እና “የሀይማኖት መሪዎቻችንን ራሳችን በራሳችን መንገድ መምረጥ እንፈልጋለን“ የሚለው ሁለት፤ ነበሩ፡፡ መንግስት ግን ጆሮውን ይዞ ፀጥ አለ… ይባስ ብሎም የሀይማኖቱን ምርጫ በቀበሌ ካላደረጋችሁ አላቸው፡፡ ማለት ብቻም አይደለም፤ በቀበሌ ውስጥ ኢማሞችን አስመረጠ… ቀጠለናም የተፈጠረውን አለመግባባት ሊያስታርቁ ላይ ታች የሚደክሙ መፍትሄ አፈላላጊዎችን አሰራቸው፡፡ እናም የጥቄዎቹን ቁጥሮች አሳደገ! ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎችን እየጠየቁ ነው… መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ አይግባ፣ የራሳችንን መሪዎች ራሳችን በራሳችን እንምረጥ፣ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎቻችን ይፍቱልን! እነዚህ ጥያቄዎች በጣም ጥቂት ናቸው፡፡ ጠያቂዎቹ ግን እጅግ በጣም ብዙ ናቸው፡፡ መላሹ ደግሞ ትንሽ እንኳ መስማት አልቻለም! ዌም ትያቄው አልገባውም፡፡ ለጥያዎቹ ምላሽ የተለያዩ ዶክመንተሪ ፊልሞችን እና የተለያዩ “ሰው ለሰው“ ድራማዎችን እያሳየ ነው… (እያሉ ያሙታል…) በመጨረሻም እንዲህ አንጎራጉራለሁ፤ እስቲ ጠይቁልኝ መንግስትን በሰዉ ይሄንን ሁሉ ጩኸት ማይሰማው ምነው!? ጥቂት ጥያቄ፣ እጅግ በጣም ብዙ ህዝብ፣ ትንሽ እንኳ የማይሰማ መንግስት! ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ዛሬም “ድምፃችን ይሰማ“ ሲሉ በአለም ዙሪያ አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡ በዛሬው ተቃውሞ፤ ከወትሮው በተለየ መልኩ፤ በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአንድ ላይ ተሰባስበው አቤት ሲሉ፣ እስከዛሬ የተቃውሞ ድምፃቸው ያልተሰማባቸው አካባቢዎችም ተቃውሞውን መቀላቀላቸው ተሰምቷል፡፡ ትዝ ይለናል… ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በመጀመሪያ የጠየቁት ሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎችን ብቻ ነበር፡፡ “መንግስት ሌላ የሃይማኖት አስተምሮ በግድ አይጫንብን እኛ እንደምን ማምለክ እንዳለብን እናውቃለን“ የሚለው… አንድ! እና “የሀይማኖት መሪዎቻችንን ራሳችን በራሳችን መንገድ መምረጥ እንፈልጋለን“ የሚለው ሁለት፤ ነበሩ፡፡ መንግስት ግን ጆሮውን ይዞ ፀጥ አለ… ይባስ ብሎም የሀይማኖቱን ምርጫ በቀበሌ ካላደረጋችሁ አላቸው፡፡ ማለት ብቻም አይደለም፤ በቀበሌ ውስጥ ኢማሞችን አስመረጠ… ቀጠለናም የተፈጠረውን አለመግባባት ሊያስታርቁ ላይ ታች የሚደክሙ መፍትሄ አፈላላጊዎችን አሰራቸው፡፡ እናም የጥቄዎቹን ቁጥሮች አሳደገ! ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎችን እየጠየቁ ነው… መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ አይግባ፣ የራሳችንን መሪዎች ራሳችን በራሳችን እንምረጥ፣ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎቻችን ይፍቱልን! እነዚህ ጥያቄዎች በጣም ጥቂት ናቸው፡፡ ጠያቂዎቹ ግን እጅግ በጣም ብዙ ናቸው፡፡ መላሹ ደግሞ ትንሽ እንኳ መስማት አልቻለም! ዌም ትያቄው አልገባውም፡፡ ለጥያዎቹ ምላሽ የተለያዩ ዶክመንተሪ ፊልሞችን እና የተለያዩ “ሰው ለሰው“ ድራማዎችን እያሳየ ነው… (እያሉ ያሙታል…) በመጨረሻም እንዲህ አንጎራጉራለሁ፤ እስቲ ጠይቁልኝ መንግስትን በሰዉ ይሄንን ሁሉ ጩኸት ማይሰማው ምነው!?
Posted on: Fri, 26 Jul 2013 18:19:24 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015