Boom time for beetroot, the new superfood: Sales up 20% in four - TopicsExpress



          

Boom time for beetroot, the new superfood: Sales up 20% in four years after claims root vegetable can help treat blood pressure and boost athletic performance ... See at ... diretu.be/994436 | በምዕራቡ ዓለም የቀይ ሥር ተወዳጅነት እየጨመረ መምጣቱ ተነገረ፡፡ እምብዛም ተወዳጅነት ያልነበረው ቀይ ሥር አሁን አሁን ሳይንሳዊ ምርምሮች የሚያስገኛቸውን ጥቅሞች መዘርዘር ከጀመሩ ወዲህ በምዕራቡ ዓለም ተወዳጅነቱ እየናረ መምጣቱ እየተነገረ ነው፡፡ ቀይ ስር በውስጡ የብረት ማዕድንና ፎሊክ አሲድ መያዙ እንዲሁም በናይትሬትና በሌሎችም አንቲኦክሲዳንቶች የዳበረ መሆኑ የደም ግፊትን ለመቀነስና ካንሰርን ለመከላከል እንደሚረዳ የምርመር ውጤቶች አረጋግጠዋል፡፡ የቀይ ስር ጭማቂ የአትሌቶችን ብቃት እንደሚጨምር የሚገልጸው ሌላው የምርምር ውጤትም የቀይ ስርን ተወዳጅነት ያናረው ሌላኛው ምክንያት ሆኗል፡፡ እነዚህ ሁሉ ተደማምረው በአጠቃላይ ባለፉት 4 ዓመታት የቀይ ስር ሽያጭ በ20 % መጨመሩ እጅግ አስደናቂ ተብሎለታል፡፡ በመሆኑም በተለይም በምዕራቡ ዓለም አነስተኛ ተወዳጅነት የነበረውና በብዛትም ለማቅለሚያነት ይውል የነበረው ቀይ ስር አሁን አሁን ግን ባሉት የጤና በረከቶች ሳቢያ በጤና ምግቦች (Health Foods) ተመጋቢያን ዘንድ ዝናው የገነነ ሆኗል፡፡
Posted on: Wed, 07 May 2014 13:30:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015