Louis van Gaal armed with £200million to revamp Manchester United - TopicsExpress



          

Louis van Gaal armed with £200million to revamp Manchester United ... See at ... diretu.be/997822 | አዲሱ የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ልዊስ ቫን ሀል በ200 ሚሊየን ፓውንድ ገበያ ሊወጡ ነው ትላንት ማንቸስተር ዩናይትድን መቀላቀላቸው ይፋ የሆነው ሆላንዳዊው አሰልጣኝ ልዊስ ቫን ሀል በአመት 6 ሚሊየን ፓውንድ የሚከፈላቸው ሲሆን ለዝውውር ገበያውም ማንቸስተርን ወደ ቀድሞው አሸነፊነቱ ለመመለስ 200 ሚሊየን ፓውንድ ተመድቦላቸዋል፡፡ ዲቪድ ሞይስን አሰናብቶ ቫን ሀልን የሶስት አመት ኮንትራት ያስፈረመው ማንቸስተር ዩናይትድ የክለቡን ተጫዋች እና ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሪያን ጊግስን ከተጫዋችነት እራሱን እንዲያገል በማድረግ የቫን ሀል ምክትል አድርገውታል፡፡ ክለቡ የ92 ክላስ አባላት የሆኑትን ፊል ኔቭል ኒኪበት ብሎም ፖል ስኮልስን በቡድኑ ውስጥ ማቆየት ቢፈልግም ግልጽ የሆነ የስራ ክፍፍል ግን አልተሰጣቸውም፣ ቫን ሀል ከአለም ዋንጫ በሁዋላ ወዲውኑ ስራ የሚጀምሩ ሲሆን እራሳቸው ግን ከወዲሁ የተጫዋች ዝውውር ሊስታቸውን ለክለቡ ማሳወቃቸው ታውቋል፡፡ ቴኒ ክሮስ፣ አርየን ሮበን፣ ማሪዮ ማንዱዚች፣ ማትስ ሀምልስ፣ ባድ ስታበር በዝርዝራቸው ውስጥ ተካተዋል፣ የ62 አመቱ ቫን ሀል የማንቸስተር የመጀመሪያው የውጭ አሰልጣኝ ሆነው ተመዝግበዋል፣ ሁሌም በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መስራት ምኞቴ ነበር ያሉት አዲሱ አሰልጣኝ እንደ ማንቸስተር ዩናይትድ ካለ ትልቅ ቡድን ጋር መስራት ለእኔ ክብር ነው ብለዋል፡፡ አዲሱ አሰልጣኝ ቫን ሀል ከሆዜ ሞሪኒሆ የእንኳን ደስ አለህ የሚል መልእክት ደርሷቸዋል፣ ቫን ሀል መጀመሪያ ቴክስት ያደረኩትኝ ለሞሪኒሆ ነበር እርሱም በፍጥነት ምላሽ ሰጠኝ እናም እኔ ባሰለጠንኩዋቸው ክለቦችና ሀገራት ስም ባርሴሎና ባየር ሙኒክ አያክስ ብሎም ሆላንድ ዝርዝር በጣም እንደሚቀና ጭምር ነግሮኛል ብለዋል፡፡ እኔ ግን ማንቸስተርንም እንዳሰለጥን ተጠራሁኝ እንጂ አልጠየቁኝም ባየር ሙኒክንም ቢሆን እንዳሰለጥን ተመረጥኩኝ እንጂ እዛም ቢሆንም አልደወልኩኝም በማለት የተናገሩት ቫን ሀል ማንቸስተርን ከመረከባቸው በፊት ጡረታ ስለመውጣት አስብ ነበር በተለይ ባለቤቴ ጡረታ እንድወጣ ትፈልግ ነበር አሁን ግን ነገሮች ተቀይረው ከኔ ጋር ወደ እንግሊዝ ትመጣለች ብለዋል፡፡
Posted on: Tue, 20 May 2014 08:05:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015