Preparations have completed for the Construction of five Airports - TopicsExpress



          

Preparations have completed for the Construction of five Airports ... See at... diretu.be/252978 | በአገሪቱ አምስት አዳዲስ አውሮፕላን ማረፊያዎች ሊገነቡ ነው ተባለ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የአምስት አዳዲስ አየር ማረፊያዎች ግንባታ በቅርብ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በድርጅቱ የሕዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወንድም ተክሌ ድርጅቱ በሽሬ እንዳስላሴ የጄነራል ኃየሎም አርዓያ አየር ማረፊያን ጨምሮ በሐዋሳ ፣ በጂንካ ፣ በሰመራና በሮቤ የመሰረተ ልማት ግንባታ በቅርቡ ይጀመራል፡፡ ግንባታቸውም የሚካሄዱት እነዚህ አየር ማረፊያዎች በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ቁጥራቸውን 21 ለማድረስ የታለመውን ዕቅድ ለማሳካት ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ የግንባታ ስራ ለመጀመር የሚያስችል ቅድመ ዝግጅቱ በአሁኑ ወቅት መጠናቀቁን የተናገሩት ኃላፊው ፥ ድርጅቱ 17 አየር ማረፊያዎች እያስተዳደረ እንደሚገኝ ተናግረዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡
Posted on: Mon, 02 Jun 2014 12:16:50 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015