ለጽንፈኛ የጀዋር ተቺዎች … (CORRECTED - TopicsExpress



          

ለጽንፈኛ የጀዋር ተቺዎች … (CORRECTED VERSION) - by Nasrudin Ousman የጀዋርን ንግግር መነሻ በማድረግ በዩ ቲዩብ እና በሌሎችም ማኅበራዊ ድረ ገፆች እጅግ በርካታ የነቀፋ አስተያየቶች ተጽፈዋል፡፡ የተወሰኑ ኢትዮጵያውያን የጀዋር “ሜንጫ” በጣም ቢያስከፋና ቢያስደነግጣቸውም ንግግሩ የፈጠረባቸውን ድንጋጤ ተቋቁመው በሰከነ አዕምሮ ከስሜታዊነት የራቀ በሳል ሐሳባቸውን አጋርተውናል፡፡ በሌላ በኩል ቁጥራቸው እጅግ በርካታ ሊባል የሚችል ኢትዮጵያውያን በጀዋር ንግግር መነሻነት ያንፀባረቋቸው ብሄርና ሃይማኖት ተኮር አስተያየቶች የእነርሱንም ዕይታ ወይም አስተሳሰብ ጤናማነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው፡፡ እነዚህኛዎቹ መድረኩ ቢሰጣቸው የጀዋርን “ሜንጫ” በ“ገጀራ” ተክተው የሁከት ጥሩንባ እንደማይነፉ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ በእኔ እምነት እንዲህ ዓይነት ሰዎች ለዚህች አገር መጻዒ ዕጣ ሸክም እንጂ ተስፋዎች አይደሉም፡፡ አንዳንዶች የጀዋርና ከእርሱ ቀጥሎ መድረክ ላይ የወጣው የአቶ ነጂብ ንግግርን በማስታከክ ለኢስላም እና ለሙስሊሞች ያላቸውን ነባር አሉታዊ ዕይታ ወይም የታመቀ ጥላቻ ተንፍሰውበታል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላለፉት አሥራስምንት ወራት እያካሄዱ የሚገኙትን የሃይማኖት ነፃነትና መብትን የማስከበር ሰላማዊ ትግልን የመጠራጠርያ ምክንያት አድርገው ወስደውታል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ለህዝበ ሙስሊሙ ሕጋዊ የመብት ጥያቄ ምላሽ ላለመስጠት በመሻት እንቅስቃሴውን ጥላሸት የመቀባት ዘመቻ ሲያካሂድ የከረመው የኢህአዴግ መንግሥት የአገር ውስጥና የባህር ማዶ ካድሬዎች ቢበዙም፣ ጥርጣሬው የተጋባባቸው የህዝበ ሙስሊሙን የመብት ጥያቄዎች ደግፈው ሲንቀሳቀሱ የከረሙ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች ቁጥርም ቀላል አይደለም፡፡ እነዚህ ወገኖች ወደ“ጠርጣሮች” አምባ የተገፉት፣ በተለይ አቶ ነጂብ ኢሳትን በመሰሉ ጣቢያዎች ከህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች ጋር በተገናኘ መግለጫ በመስጠት ስለሚታወቅ፣ የህዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊ ትግልና አቶ ነጂብን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ አድርገው ስለተረዱ ይመስለኛል፡፡ የህዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊ ትግል በቅርበት የሚከታተሉና ለትግሉም አወንታዊ ምልከታ ያላቸው ወገኖች አቶ ነጂብ በዚያ መድረክ ላይ ያንፀባረቀውን ሐሳብ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ትግል መሪዎች ሐሳብ አድርገው ከወሰዱት ተሳስተዋል፡፡ የአቶ ነጂብ ሐሳብ የአቶ ነጂብ ነው፡፡ ሐሳቡን የሚጋሩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አይኖሩም አልልም፡፡ ነገር ግን ጀዋርም ሆነ ነጂብ ያንፀባረቋቸው ሐሳቦች (በሰማሁት መጠን) የህዝበ ሙስሊሙ የሃይማኖት ነፃነትን የማስከበር ሰላማዊ ትግል መነሻም መድረሻም እንዳልሆኑ በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ፡፡ ዘግይቶ ያነበብሁት የጀዋር ማብራሪያ ደግሞ፣ ‘ሜንጫ’ን የጠቀሰበት ዐውድ፣ “ዋ እንዲህ ታደርግና በሜንጫ ነው የምልህ!” ከማለት ያልተለየ ተለምዷዊ ቀበሌኛ አነጋገር መሆኑን አስረድቶኛል፡፡ የጀዋርን ማብራሪያ እንዳነበብሁ በመጀመርያ ትዝ ያለኝ ቀደም ብዬ ከጀዋር ማብራሪያ ጋር በአባሪነት ‘ሼር’ ያደረግሁት የባሻ አሸብር ዱላ ሲኾን፣ ሌላው ትዝ ያለኝ ግንቦት 7፣ 1997 ምሽት “ከነገ ጀምሮ ጣቱን የሚቀስር ጣቱ ይቆረጣል!” የሚለው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትራችን ንግግር ነው፡፡ … የእርሳቸው እንዳውም የቀበሌኛም አልነበረም፡፡ በሰኔ 1997 እና በጥቅምት 1998 ጣት ከመቁረጥ አልፈው ታዳጊ ሕፃናትን ጨምሮ የ196 ገደማ ወጣቶች ህይወት እርሳቸው በሚያዝዙት ፌደራል ፖሊስ ጥይት አስቀጥፈዋል፡፡ የህዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊ ትግል በጽናት ሲደግፉ የቆዩ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖቻችን የሙስሊሙን ህዝብ ሦስት ግልፅ ጥያቄዎች ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ፣ በጀዋር አልያም በአቶ ነጂብ ንግግር ሳቢያ ደርሰው “የኢህአዴግ ‘የእስላማዊ መንግሥት’ ፕሮፖጋንዳ እውነት ይሆን እንዴ?!” የማለት ዝንባሌ ማሳየታቸው አስገርሞኛል፡፡ በአንድ በኩል፣ አስተያየታቸው የጀዋር “ሜንጫ” ከፈጠረባቸው ከባድ ድንጋጤ የመነጨ ሊሆን ይችላል ብዬ አስቤአለሁ፡፡ በሌላ በኩል ግን፣ እነዚህ ወገኖች ለህዝበ ሙስሊሙ ሰላማዊ የመብት ትግል ሲሰጡ የቆዩት ድጋፍ በመርኅ ላይ የተመሠረተ መሆኑ አጠራጥሮኛል፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚገኙ ሙስሊም ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሃይማኖት ነፃነትና መብትን የማስከበር ትግል የሚሰጡት ድጋፍ ከመርኅ ይልቅ “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው” በሚል እሳቤ ላይ ብቻ የተመሠረተ ከሆነ፣ ከረዥም ጊዜ አኳያ ምንም ፋይዳ አይኖረውም፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ ሙስሊም ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን የሃይማኖት፣ የእምነትና የአስተሳሰብ ነፃነት መከበር ለሙስሊሙም ሆነ ለክርስቲያኑ፣ በአጠቃላይም ለአገሪቱ ዘላቂ ሰላምና ብልፅግና ጠቃሚም አስፈላጊም ነው ብለው እስካላመኑ ድረስ ፀረ ኢህአዴግ ድምፆች እንዲበራከቱ በመሻት ብቻ ለሙስሊሙ ትግል ድጋፍ ከሚሰጡ ዝም ቢሉ ነው የሚሻለው፡፡ እየደረሰብን ያለው የሃይማኖት ነፃነትና መብት ጥሰት እንዲሁም በህዝበ ሙስሊሙ ላይ እየከፋ የመጣው የመንግሥት ግፍና በደል አሳስቧቸው ትግላችንን የሚደግፉ ወገኖቻችን መኖራቸውን አንጠላም፡፡ በአንፃሩ ዛሬም የሆነ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ዜግነት ለመጠራጠር የሚቃጣቸው መኖራቸው ግን … እንደው ግርም ይለኛል፡፡ … አላህ (ሱ.ወ.) ሃይማኖትን እና ብሄርን መሠረት ያደረገ ጥላቻን ከላያችን ላይ ያንሳልን፡፡ አሚን፡፡
Posted on: Sun, 21 Jul 2013 03:37:14 +0000

Trending Topics



ns working with a company with SFI reliable
iv class="sttext" style="margin-left:0px; min-height:30px;"> Statement as of 4:16 AM EDT on August 04, 2013 A cold front and
t:30px;"> Cyber Monday Fire Extinguisher, Wet Chemical, K, KBlack Friday

Recently Viewed Topics




© 2015