ሰላም በፋቃዱ - TopicsExpress



          

ሰላም በፋቃዱ እኔእኮከምንምበላይግርምየሚለኝነገርቢኖርአንዳንዶች “ ስለምን የመንግስትን መጥፎነት ብቻ ትናገራላቹ” የሚሉት ፈሊጥ ነው… ሕይ ነገር በተደጋጋሚ ለመናገር ሞክሪያለው፡፡ እሺሁላችንም ከጭፍን ደጋፊነትም ሆነ ከጭፍን ተቃዋሚነት በስተጀርባ በመሆን ያለምንም አድሎዋዊነት እውነታውን እንናገር፡፡ እውነት የኢሀዴግ መንግስት አስተዳደር ከአሉታዊ እና ከ አዎንታዊጎኑ ይበልጥ ጉልቶና ገዝፎ የሚታየው ሀቅ የቱይሆን? እንዴ!!!እንዴት ሆኖ ይሆን የአምላክ አምሳያው የሰው ልጅ ከቁሳዊ ነገር ሊበልጥብንየሚችለው? እንዴትስ ቢሆን ነው ነጻ አስተሳሰብ በሌለበት ማህበረሰብ ውስጥ እድገት አለ ልንል የምንችለው? የናንተን አላውቅም ለኔግን የ 100 ፎቆች ግንባታ ቀርቶብኝ አንድዜጋ ሰብአዊመብትን ያለገደብ የሚጠቀምባትን ሀገር መርጣለው….የአባይ ግድብ ከሚገደብ ቅድሚያ የንጹሀኑ ( እስክንድርነጋ ፤አቡወከር ፤ እርዩት፤በቀለገርባ…)የነጻነት ኑሮን እመርጣለው…ከባቡር መስመር ይልቅ ዜጎችያለፍርሀት የመሰላቸውን የሚናገሩበት የሚጽፉበት ሀሳባቸውን ያለገደብ የሚያንሸራሸሩበት ሀገርማግኘትን በቅድሚያእሻለው… ለምን? ብትሉኝ…የሰው ልጅ ከምንምአይነት ቁሳዊ ነገር አይበልጥብኝምና በተጨማሪም ነጻ አስተሳሰብ ያለው ትውልድ እውነተኛውን የኢትዪጵያ ህዳሴ ጎህ ይቀዳልበማለትአምናለው፡፡ ታዲያ እንዴት ቢሆን ነው ከህያው ፍጡር ለቁስ ቅድሚያ ለሰጠው የኢሀዴግ መንግስት አዎንታዊ ጎኖች የመናገር አቅም የሚኖረኝ? እረ እንዴትስ ቢሆን ነው ፍቅር ከ ገንዘብ የሚበልጥብኝ? ይሕን መሰልጥያቄ ጠያቂ ወገኖቼ ሆይ… ምናልባት ዛሬ ደልቶቹ ወታቹ በሰላም ስለገባቹ የወገን ቁስልሳይታይቀርቶ በነጻነት ሀገርየምትኖሩ የሰላም ሀገር ዜጎችሊመስላቹ ይችልይሆናል፡፡ነገር ግን እርግጠኛ ሁኑ ወይንም አመኑኝ በአንባገነን ስርአት ውስጥ በአንዲት ወቅት ብር የማይገዛውን የማይለወጠውንና የማይሻረውን ሕሊናዊ ነጻነትና ፍትህ ፈልጋቹ ማጣታቹ አይቀርም ያኔ ግን በራስ ሲደርስ ከቁስአካል ነጻነትን ተግታቹ እንደምትሾት የአሁኖ ትንቢቴ ነች፡፡ ሰላምበፍቃዱ!!
Posted on: Mon, 02 Sep 2013 07:11:26 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015