ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድርድር ጀመሩ - TopicsExpress



          

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድርድር ጀመሩ :: ብሄራዊ ጥቅም የኤርትራ የመደራደሪያ አጀንዳ ነው:; የኢትዮጵያ ግን አልታወቀም!! የኤርትራ መንግስት ባለስልጣናት በሰጡት መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ የኤርትራ መንግስት የሚያቀርብወን ሃሳብ በፍቃደኝነት ለመቀበል እና ለመፈጸም በመስማማቷ በአዲስ አበባ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የኤርትራ ወኪል የሆነው ግርማ አስመሮምን ለድርድር መወከላቸውን አስታውቀዋል:: እርትራ አሁን እያረቀቀች ባለችው አዲስ የውጪ ፖሊሲ ድንጋጌ መሰረት የፖሊሲው ሙከራ የመጀመሪያ ዙር በኢትዮጵያ ሲሆን ከዛ ወደ ሌሎች ሃገሮች እንደሚቀጥል ባለስልታናቱን የጠቀሱ ምንጮች ተናግረዋል:; በሶማሊያ በግብጽ በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን ያሉ ውጥረቶችን ለመፍታት በግንባር ቀደምትነት ለመስራት እድሉ እንዲሰጣትም እርትራ ጠይቃለች:: ከኢትዮጵያ ጋር የምታደርገው ድርድር ብሄራዊ ጥቅሟን የጠበቀ እንደሚሆን የተናገሩት ባለስልታናቱ ወደቡን በኪራይ መስጠት የባድመ እና ሌሎች መሬቶችን መረከብ የገንዘብ ዝውውር እና ምንዛሬን በተመለከተ መደራደር እንደምትፈልግ አስታውቀዋል:: እንዲሁም አሉ ስለሚባሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተጣጠፍ እንደሚነጋገሩ አውስተዋል::የአልሸባብም ጉዳይ ይነሳል:: እርትራ በአሁኑ ሰአት የተባበሩት መንግስታት ማእቀብ በጎረቤት አገሮች ላይ ያላት የአፍራሽነት ሚና የሃገሪቱ ኢኮኖሚ መድቀቅ የውሃ እና የመብራት አለመኖር ሃገሪቷ እንደሃገር መኖር እያቃታት መምጣቷ ወደ ድርድር እንዳመጣት ምንጮቹ ጠቁመዋል::
Posted on: Fri, 02 Aug 2013 19:09:16 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015