የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን - TopicsExpress



          

የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን ከአንድ ሳምንት በዃላ በሴካፋ ለመሳተፍ ወደ አዘጋጇ አገር ኬንያ ይጓዛል። ወድድሩን አሰልጣኝ ሰውነት የሚያደርጉት በአብዛኛው በአለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ የመጫወት እድል ባላገኙት ተጨዋቾች እንደሚሆንም ነው የተናገሩት። ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለሴካፋ ዝግጅቱን ነገ እንደሚጀምር የተገለፀ ሲሆን ፥ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከአዘጋጇ ኬንያ ጋር ህዳር 18 ያደርጋል። ኢትዮጵያ የሴካፋ ዋንጫን 4 ጊዜ ማሸነፏ ይታወሳል። ምንጭ Ethio Kickoff
Posted on: Tue, 19 Nov 2013 10:40:59 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015