የፌስ ቡክ ሴቶች / አቤል - TopicsExpress



          

የፌስ ቡክ ሴቶች / አቤል በሬቻ/ ያየሁትን እናገራለሁ ካልታየህ እለፈው ከታየህ ሃሳብ ጨምርበት ከተናደድክ ደሞ ቁጣህን ሳታበርድ በውስጥ መልክት አናግረኝ ፤ ከዚህ የተለየ ሃሳብ ካለህ ግን ጨረታውን በወደድከው መንገድ ተጫረተው ፡፡ ብዙ አይነት ሴቶች አሉ እዚህ የጉድ መንደር ፌስ ቡክ ውስጥ አንዳንዷ ታስቃለች ፤ አንዳንዷ ታስደንቃለች ፤ አንዳንዷ ታሳዝናለች ፤ አንዳንዷ ደግሞ ኑሮ በዘዴ ስልትን ትከተላለች ፡፡ የቻልኩትን ያህል ላሳይክ ብዙ ናቸው ግን ጥቂቶቸቹን ብቻ ልንገርህ ፡፡ 1.. ባለ ፎቶቹ ቺኮች እነዚህ ሴቶች በአንድም በሌላም ምክንያት ፌስ ቡክን እንደ ፎቶ አልበም የሚጠቀሙ ናቸው ፡፡ በሳምንት ከሁለት እስከ ሶስት የሚደርስ ፎቶ በመለጠፍ ይታወቃሉ ፡፡ ስለነዚህ ሴቶች ሳስብና ስጠረጥር ብዙ ጊዜ ሚጠብሳቸው ፎቶ የሚያነሳቸው ሰው ይመስለኛል ፡፡ እቤታቸው ያጡትን የቆንጆ ነሽ ሙገሳ ፌስ ቡክ ላይ ስላገኙ ቆንጆ የመሆናቸው ማረጋገጨቻ ፌሽ ቡክ ብቻ ነው ፡፡ 2.. ባለ ሃይማኖቶቹ ቺኮች እነዚህ ደሞ ገዳሙን ፤ መጅሊሱን ፤ ቸርቹን ፌስ ቡክ ላይ አምጥተው ያነፁ ናቸው ፡፡ ሃይማኖታዊ ቀናትን የሚያከብሩት እዚሁ ፌስ ቡክ ላይ ነው ፡፡ስለ ሀይማኖት መከራከር ፤መጨቃጨቅ ሰውን መነዝነዝ ያበዛሉ ምክንያታዊ ሰዎች አይደሉም ፤ እንደ ሃይማኖተኝነታቸው አስተምሮና ህሳቤ ጨዋነት ከእነርሱ ይጠበቃል ነገር ግን ለሃይማኖታቸው ባላቸው ቀኛይነት የተነሳ አይሆኑ ስህተት ሲሳሳቱ ይታያሉ ፡፡ ሚሳተፉበት ግሩፕ ሃይማኖታዊ ጭቅጭቅ ያለበት ነው ስራቸው ሁሉ ከሃይማኖት ጋር ስለሚያያዝ ያስፈራሉ ፡፡ 3.. ጀንጃኝ ቺኮች አይን አውጣዎች ናቸው በትርፍ ሰዓታቸው ወንድ ወንድ የሚጫወቱ አይነቶች ናቸው ፡፡ በማይረባ ምክንያት ከወንድ ጋር በውስጥ መስመር ወሬ ይጀምራሉ ከዛ ማባርያ የላችም ፡፡ ‹‹ ሰራተኛ ነህ ተማሪ›› በሚል ጥቃቅንና አነስተኛ ወሬ ወሬያቸውን ይጀምራሉ ከዛ የሚችላቸው የለም ፡፡ ወሬያቸው ደብሮአቹ ከዘጋቸቿቸው ከነሱም ብሶ ሆድ ይብሳቸዋል ፤ያዝናሉ ፤ ያኮርፋሉ፡፡ በፌሰ ቡክ ያወቃቿቸው ሳይሆን በትዳር የተጣምራቿቸው እስኪመስላቹ ድረስ ነው የሚያሰለቹት ፡፡ 4... ባለ ፒትሮን ቺሎች እነዚህ ደሞ እንደ ጢንዚዛ እዛም እዚም የሚበሩ ማረፍያ የሌላቸው ከሁሉ ጋር መወዳጀት የሚያምራቸው ናቸው ፡፡ የተወደደን ይወዳሉ የተጠላን ይጠላሉ ፤ ሰው ያወገዘውን ያወግዛሉ በሰዎች ድጋፍ እንጂ በራሳቸው ጉልበት መቆም የማይችሉ ናቸው ፡፡ አላማቸው አለው…. አትርሱኝ የማለት ያክል እንጂ ሚረባና ተጨባጭ ነገር የላቸውም፡፡ ሁሉም ሰው ፎቶ ላይ አሉ ፤ ሁሉም ሰው ፅሑፍ ላይ አሉ ፡፡ የሚያደርጉትን ነገር የሚያደርጉት ተደግፈህ እለፍ በሚል ፖሊሲ ነው ፡፡ መቀጠል ይቻላል ብዙ ጥሩም ሴቶች ግን እንዳሉ አረሳሁም ለማንሳት ያህል እነዚህን ብቻ ማንሳት ፈለኩ እንጂ
Posted on: Wed, 02 Oct 2013 18:40:22 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015