Chinese GCL Poly to invest 10 billion dollars in Ethiopia ... See - TopicsExpress



          

Chinese GCL Poly to invest 10 billion dollars in Ethiopia ... See at .... diretu.be/342638 |የቻይናው ጂ ሲ ኤል ፖሊ ኩባንያ እስከ 10 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ ሊያካሂድ ነው ተባለ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደዘገበው የቻይናው ጂ ሲ ኤል ፖሊ ኩባንያ ለጋዝና ፔትሮሊየም ማዕድን ልማት ኢንቨስትመንቱ የኢትዮጵያ መንግስት ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ገለጸዋል። ፕሬዝዳንት ሙላቱ በኩባንያው ፕሬዝዳንት ዋንግ ሊ የልኡካን ቡድንን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ኩባንያው በጋዝና በፔትሮሊየም ማዕድን ልማት ዘርፍ የሚያደርገው ኢንቨስትመንት ለልማት እጅግ አስፈላጊ ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ሙላቱ፥ የፔትሮሊየም ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። ኩባንያው የጋዝና ፔትሮሊየም ማዕድን ልማትን ጨምሮ በግብርና፣ በመሰረተ ልማት፣ በሆቴልና ገበያ ማዕከላት ግንባታ መዋዕለ ንዋዩን ለማፍሰስ ፈቃድ ወስዶ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ የልኡካን ቡድኑን የመሩት ዋንግ ሊ ከውይይቱ በኋላ እንደገለፁት፥ የተደረገው ውይይት በጋዝና ፔትሮሊየም፣ ሆቴል፣ ግብርና፣ ህንፃ ስራና ቱሪዝም ዘርፎች ለመስራት ዕድል የፈጠረ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማ ዘመናዊ ሆቴልና የገበያ ማዕከላት ለመገንባት ዕቅድ ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል ። ኩባንያው በኢትዮጵያ ለሚያከናውነው ጠቅላላ ኢንቨስትመንት ከ8 እስከ 10 ቢልዮን የአሜሪካን ዶላር እንደሚያስፈልገው ተጠቁሟል። ለተጨማሪ ....diretu.be/342638
Posted on: Thu, 08 May 2014 16:35:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015