#Ethiopia #Humanrights ጅሃዳዊ ሃረካት ምን - TopicsExpress



          

#Ethiopia #Humanrights ጅሃዳዊ ሃረካት ምን ያህል እንዳነታረከን ታስታውሳላችሁ? ኢሰመጉ ስለጅሃዳዊ ሃረካት ዶክመንተሪ ይህንን መግጫ አውጥቶ ነበር፡፡ ጥር 28/2005 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ራድዮ ድርጅት በፌደራል ፖሊስ እና በብሄራዊ ደህንነት እና ፀጥታ ባለስልጣን የተዘጋጀ ዘገባዊ ፊልም ለህዝብ ማቅረቡ ይታወቃል። የዶኩመንታሪዉ ይዘት በአሁኑ ሰዓት ከመስከረም 15/2005 ዓ.ም ጀምሮ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአሸባሪነት ወንጀል ተከሰዉ ፍርድ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙትን ተከሳሾች በተለያ የሽብር እና የአመፅ ተግባራት ያላቸዉ ተሳትፎ እና ዝግጅት ላይ የሚያጠነጥን ነዉ። ጥናታዊ ፊልሙ እነዚህ የተከሰስንበትን ወንጀል አልፈፀምንም ብለዉ በፍርድ ቤት በመከራከር ላይ የሚገኙትን ተጠርጣሪዎች ከናይጄርያዉ ቦኮ ሃራም፣ ከሶማልያዉ አልሸባብ እና ከአልቃይዳ ጋር በማመሳሰል የሽብር ወንጀል ለመፈፀም ሲያሴሩ እና ሲዘጋጁ እንደነበር ይገልፃል። ፊልሙ የብሄራዊ ደህንነት እና ፀጥታ ባለስልጣን እነዚህን ተጠርጣሪወች ለብዙ ዓመታት ለወንጀል ዝግጅት ሲያደርጉ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ቢገልፅም እነዚህ የወንጀል ዝግጅቶች ስለመደረጋቸዉ የቀረበዉ ማስረጃ ግን ተከሳሾቹ በራሳቸዉ ላይ ሲመሰክሩ የሚያሳይ ቃለ ምልልስ ብቻ ነዉ።
Posted on: Mon, 17 Jun 2013 12:02:10 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015