Ethiopia ignores repeated calls for dam negotiations: Egypt FM - TopicsExpress



          

Ethiopia ignores repeated calls for dam negotiations: Egypt FM .... See at ... diretu.be/886674 | ግብጽ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያ ለድርድር ዝግጁ አይደለችም አለች፡፡ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናቢል ፋህሚ እንዳሉት ከሆነ ግብጽ ለኢትዮጵያ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በተደጋጋሚ የድርድር ጥያቄ ብታቀርብም ከኢትዮጵያ በኩል ትክክለኛ ምላሽ አልተገኘም፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከአልአህራም ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት ግብጽ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጉዳይ በምንም አይነት እነደማትዘነጋው እና እንደምትከታተለው ገልጸዋል፡፡ ግብጽ ፣ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉት በድርድር በሚመጣ ስምምነት ነው ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በድርድሩ ዙሪያ እርስ በርሱ የሚጣረስ ሃሳብ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ከግብጽ ጋር የመወያየት ሃሳብ እንዳለው እና የኤክስፐርቶች ቡድን በሰጠው ሃሳብ ላይ ተመርኩዞ ተጀምሮ የነበረው የሶስትዮሽ ውይይት እንዲቀጥል ፍላጎቱ መሆኑ በተደጋጋሚ የገለጸ ቢሆንም የግብጽ መንግስት በተለያዩ ግዚያት ያቀረባቸውን የተለያዩ የአረብ ሀገራት በአደራዳሪነት እንዲሳተፉ እና ሌሎች የድርድር መንገዶችንውድቅ ማድረጉ የሚታወቅ ነው፡፡ See at ... diretu.be/886674
Posted on: Wed, 14 May 2014 21:25:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015