Ethiopia to launch SMS fundraising campaign to fight Ebola - - TopicsExpress



          

Ethiopia to launch SMS fundraising campaign to fight Ebola - የአፍሪካ ህብረት እና ኢትዮጵያ በአፍሪካ የኢቦላን ስርጭት ለመግታት የአጭር መልእክት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዛሬ ይጀምራሉ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር የኢቦላ ቫይረስን ለመግታት የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ አጭር መልእክት መጀመሯን የአፍሪካ ህብረት አስታውቋል፡፡ በአንድ የአጭር መልእክት 1 የአሜሪካ ዶላር መለገስ በሚያስችል መልኩ የተቀረጸው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙ ለባለሞያዎች ስልጠና ለመስጠት እና መሰል የኢቦላ መከላከል ስራዎችን ለማከናወን ይረዳል ተብሏል፡፡ የገቢ ማሰባሰቢያው ዛሬ ታህሳስ 11 – 2007 በአፍሪካ ህብረት ትንሽዋ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል፡፡
Posted on: Sat, 20 Dec 2014 08:30:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015