Ethiopias teff poised to be next big super grain | ጤፍ - TopicsExpress



          

Ethiopias teff poised to be next big super grain | ጤፍ ኢትዮጵያ ከቡና ቀጥሎ ለዓለም የምታበረክተው የእህል ዘር እየሆነ ነው…ይላል በቅርቡ የብሪታኒያው ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ ይዞት የወጣው ዘገባ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ 6.3 ሚሊየን ገበሬዎች የሚያመርቱት እህል ነው - ጤፍ፡፡ በሀገራችን ከታረሰው መሬት 20% ያህሉ የጤፍ ማሳ ነው፡፡ በአጠቃላይ ጤፍ በጣሙን ተወዳጅ የሆነ ኢትዮጵያዊ የእህል ዘር ነው፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜያት ድረስ ግን ጤፍ ከኢትዮጵያ ውጪ በኢትዮጵያ የዳያስፖራ ማህበረሰቡ ዘንድ ብቻ ነበር ተወዳጅነቱ፡፡ አሁን አሁን ግን እነዚያ የጤፍ ቅንጣቶች በበርካታ ንጥረ ነገሮች የዳበሩና እንደ ግሉተን ያሉት ደግሞ ወስጡ የሌሉ መሆናቸው እየታወቀ ሲመጣ በተለይም በምዕራቡ ዓለም የጤና ምግቦች (Health Foods) ተጠቃሚው ማህበረሰብ ዘንድ ዋንኛ ምርጫ እየሆነ መጥቷል፡፡ በካልሲየም፣ ብረት እና ፕሮቲን የበለጸገው የጤፍ ዱቄት በተለያዩ የአውሮፓና የአሜሪካ ሀገራት የተመረጡ ሱቆች ውስጥ መሸጥ ከተጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ለምሳሌ ያህል ለንደን ውስጥ ያለ አንድ ሱቅ 1 ኪሎ ግራም የታሸገ የጤፍ ዱቄትን በ222 ብር ዋጋ እየሸጠ ይገኛል፡፡ በሀገራችን ካሉ የእህል አይነቶች ከስነ ምግብ ጠቃሚነቱ አንጻር በጣሙን ዋጋ ያለው እንደሆነ የሚነገርለት ጤፍ፣ ከዳቦና ፓስታ አንስቶ እስከ ፒዛ መስሪያነት ድረስ ስንዴን መተካት እንደሚችልም ታውቋል፡፡ ይህ የጤፍ ዓለማቀፍ ተወዳጅነት ግን በአስር ሚሊየኖች ለሚቆጠረው ኢትዮጵያዊ የጤፍ ተመጋቢ ህዝብ የሚያፈነድቅ ዜና እንዳይደለ ግልጽ ነው፡፡ ምንም እንኳ የኢትዮጵያ መንግስት ከእ.ጎ.አ 2006 አንስቶ ጤፍ ወደ ውጭ መላክን ቢያግድም አሁንም የጤፍ ዱቄት ወደ ውጭ እንደሚላክ ይታወቃል፡፡ ከውጭ ምንዛሪው ባሻገር ይህ ጉዳይ የጤፍን ዋጋ እያናረው የሀገሪቱን ተጠቃሚ እንዳይጎዳ ያሰጋል፡፡ ለጤፍ አምራቹ ገበሬም ቢሆን፣ የጤፍ በውጪው ዓለም ተፈላጊ መሆን መልካም ዜና ነው ማለት አይቻልም የሚሉት ብዙዎች ናቸው፡፡ ለዚህም የሚጠቅሱት ምሳሌ አሁን ዓለማቀፍ የሆነው የቦሊቪያና ፔሩው ክዌኖኧን ምርት የፈጠረውን ቀውስ እና ከእህሉ ምርት ገበሬው ሳይሆን የውጪው አመላላሽ ነጋዴ ብቻ ተጠቀሚ መሆኑን ነው፡፡ ኢትዮጵያዊው የግብርና ሳይንቲስት የሆነው ረጋሳ ፈይሳም ያለጥናት የውጭ ሀገራትን ፍላጎት ብቻ ተከትሎ የሚደረግ እርማጃ ብዙ ያስከፍለናል ይላል፡፡ ዝርዝር መረጃውን ➤➤➤ diretu.be/729455
Posted on: Thu, 23 Jan 2014 14:00:39 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015