Suit filed after bus driver calls Ethiopian 11-year-old - TopicsExpress



          

Suit filed after bus driver calls Ethiopian 11-year-old monkey...See at ... diretu.be/968632 | የ11 ዓመቷን ኢትዮጵያዊት ታዳጊ በተደጋጋሚ ዝንጀሮ በማለት የሰደበው እስራኤላዊው የአውቶብስ ሾፌር ተከሰሰ፡፡ ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች የተወለደችው እስራኤላዊቷ የ11 ዓመት ታዳጊ ወደ መዋኛ ቦታ በተደረገ ጎዞ ላይ በተደጋጋሚ በጓደኞቿ ፊት ዝንጀሮ ሲል የሰደባትን የትምህርት ቤቱን አውቶብስ ሾፌር መክሰሷ ተሰምቷል፡፡ ሾፌሩ በአውቶብሱ ማይክራፎን በመጠቀም “አንቺ ከኋላ የተቀመጥሽው ዝንጀሮ” ሲል እንደሰደባትና፣ ታዳጊዋ ከአውቶብሱ ወርዳ ቦርሳዋን እያወረደች ባለችበት ወቅትም “የታለች ዝንጀሮዋ…” ማለቱ በክሱ ላይ ተጠቅሷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ታዳጊዋ ወደ አውቶብሱ ስትመለስም “መጣሽ…ሁለተኛ በእኔ አውቶብስ ላይ እንዲህ መሆን አትችይም…በቤተሰቦችሽ ቤት የፈለግሽውን ማድረግ ትችያለሽ…ለነገሩ እነሱም ዝንጀሮ አይደሉ…አብራችሁ ወደ እንስሳ መጠበቂያ ትሄዳላችሁ” ሲል በጓደኞቿ ፊት ሰድቧታል፡፡ የ5 ዓመቷ ታዳጊ ያቀረበችውን አቤቱታ የተመለከተው የፍትህ ሚንስትር የህግ ድጋፍ ክፍል ክሱን ለእየሩሳሌም ማዘጋጃ ቤት ችሎት አቅርቧል፡፡ See at.... diretu.be/968632
Posted on: Wed, 30 Apr 2014 18:00:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015