Suspects charged with attempting to establish Islamic state given - TopicsExpress



          

Suspects charged with attempting to establish Islamic state given guilty verdict | Read More at.....goo.gl/as1Xlz | በኢትዮጵያ እስላማዊ መንግስት ለመመስረት ጥረት አድርግዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሶስት ግለሰቦች ወንጀለኛ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ የጂሀድ ጦር ስልጠና በመውሰድ በኢትዮጵያ እስላማዊ መንግስት ለመመስረትና የሽብር ጥቃት ለማድረስ ሞክረዋል በሚል ክስ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ አሊ አድሮስ ሞሀመድ፣ ሞሀመድ ሼሪፍ አህመድ እና ሞሀመድ አልሚ የሚባሉ ሲሆኑ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ተጠርጣሪዎች ነዋሪነታቸው ለንደን የነበረ ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ ከሀርጌሳ መምጣቱን የፋና ዘገባ ያመለክታል፡፡ ግለሰቦቹ ድርጊታቸውን ሙሉ ለሙሉ ያመኑ ሲሆን ጁማት ከተባለው የጂሀዲስት እስላማዊ ቡድን ጋር በድብቅ ግንኙነት እንደነበራቸውና ከሶስት አመታት በፊት ወደ የመን በማቅናት ከኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባት ጋር በመገናኘት የሽብር ስራውን ለመስራት ተስማምተዋል ሲል የፋና ዘገባ ይተነትናል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ በኋላ ጥቃቱን ለማድረስ በእቅድ ላይ እንዳሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ በቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት አሊ አድሮስ የተባለው ተጠርጣሪ ሁለቱን ተጠርጣሪዎችን ወደ አዳማ በማምጣት በዛ የቆዩ ሲሆን ወደ ኬንያ በማቅናትም የጂሀድ ጦር ስልጠና ወስደዋል፡፡ አሊ አድሮስ የተባለው ተጠርጣሪ በርካታ የስልክ ንግግሮችና የጥቃት መመሪያዎችን ሲቀበል ቆይቷል፡፡ በመሆኑም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ችሎት በዋለው ችሎት የፅሁፋና የቃል ማስረጃዎችን እንዲሁም የአቃቤ ህግ ምስክሮችን በመስማት ሶስቱን ተጠርጣሪዎች ወንጀለኛ ሆነው አግኝቷቸዋል፡፡ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት
Posted on: Fri, 12 Dec 2014 10:30:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015