Tanzania calls for Nile water agreement to be reviewed ... See at - TopicsExpress



          

Tanzania calls for Nile water agreement to be reviewed ... See at ... diretu.be/239674 | የዓባይ የትብብር ማዕቀፍ ግብፅን የሚጎዳ በመሆኑ እንዲከለስ የታንዛኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጠየቁ የኢንቴቤው ስምምነት በመባል የሚታወቀው የዓባይ ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ግብፅን የሚጎዳ አንቀጾችን የያዘ በመሆኑ፣ እንዲከለስ ሲሉ የታንዛኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአገራቸውን ፓርላማ ጠየቁ፡፡ የታንዛኒያ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር በርናርድ ካሚለስ ሜቤ ለታንዛኒያ ፓርላማ ላኩት በተባለ ደብዳቤ፣ የታንዛኒያ መንግሥት በዓባይ የትብብር ማዕቀፍ ውስጥ ስለ ፍትሐዊ የውኃ ክፍፍል የሚያነሳው ክፍል በድጋሚ ሊከለስ ይገባል ብሎ ያምናል ማለታቸውን የቱርክ ዜና ወኪል ዘገባ ያስረዳል፡፡ ሚኒስትሩ ባለፈው ሳምንት ለፓርላማው በላኩት ደብዳቤ ገለጹት እንደተባለው ከሆነ የታንዛኒያ መንግሥት የትብብር ማዕቀፍ ስምምነቱ ፈራሚ ቢሆንም የዓባይን ውኃ በእኩልና በፍትሐዊ መንገድ የተፋሰሱ አገሮች መጠቀም አለባቸው የሚለው የትብብር ማዕቀፉ ክፍል፣ ግብፅ በረሃ ላይ የተቆረቆረች አገር መሆኗን ያላገናዘበ በመሆኑ በዚሁ አግባብ ሊከለስ ይገባል ብለዋል፡፡ See at ... diretu.be/239674 ወድ የድሬቲዩብ ወዳጆች የዕርሶ አስተያየት ምንድነው? ላይክና ሼር ያድርጉ
Posted on: Sun, 01 Jun 2014 23:00:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015