The Agency to Prepare Question Bank ... See at ... - TopicsExpress



          

The Agency to Prepare Question Bank ... See at ... diretu.be/356247 | የፈተና ጥያቄዎች ባንክ ሊቋቋም ነው ተባለ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ የብሄራዊ ፈተና ጥያቄዎችን አስቀድሞ በማዘጋጀት ለማስቀመጥ የሚያስችል የጥያቄ ባንክ ሊያዘጋጅ መሆኑን ኤፍቢሲ ዘግቧል። ዘገባው የኤጀንሲውን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን ዱሬሳ ጠቅሶ እንዳመለከተው የጥያቄ ባንኩ ኤጀንሲው በማንኛውም ጊዜ በየትኛውም የትምህረት አይነት በርካታ ዝግጁ የሆኑ ጥያቄዎች እንዲኖሩት የሚያስችለው ነው። ይህ ደግሞ በየአመቱ ለጥያቄዎች ዝግጅት የሚያስፈልገውን የሰው ሃይልና ወጪ ለመቆጠብ ያስችላል ተብሏል። በተጨማሪም በማንኛውም ጊዜ ብሄራዊ ፈተናን መስጠት ቢያስፈልግ ኤጀንሲው ዝግጁ ሆኖ እንዲገኝ ያግዘዋል። የጥያቄ ባንኩ በስራ ላይ ሲውልም በአንድ የትምህርት አይነት እስከ 5 ሺህ የሚደርሱ ተቀማጭ ጥያቄዎች ኤጀንሲው እንዲኖሩት ያስችለዋል ነው ያሉት አቶ ዘሪሁን ። በርካታ ያደጉ ሀገራት አሰራሩን ለረጅም አመታት የተጠቀሙበት ሲሆን በኢትዮጵያም ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑ ተጠቁሟል።
Posted on: Sat, 17 May 2014 10:00:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015