ሜሮን እባላለው የ22 ዓመት ወጣት ነኝ፡፡ - TopicsExpress



          

ሜሮን እባላለው የ22 ዓመት ወጣት ነኝ፡፡ ቤተሰቦቼ ሞልቶ የተረፋቸው ከሚባሉት የሚመደቡ ናቸው፡፡ ብቸኛ ልጅ ስለሆንኩ አሞላቀው ነው ያሳደጉኝ የምፈልገውን ነገር ያሟሉልኛል፡፡ አባቴ በእኔ ላይ በጣም ቁጥጥር ያበዛበኛል ከቤተሰብ ጋር ካልሆነ በጭራሽ ከቤት መውጣት አይፈቀድልኝም፡፡ ቤት ውስጥ የቁም እስረኛ ነኝ ማለት እችላለው፡፡የአባቴ ፍላጎት ጥሩ ደረጃ ደርሼ በቤተሰብ በኩል በሚመጣ ጋብቻ መዳር ነው፡፡ ቤት ዉሰጥ ከብቸኝነት የሚያላቀኝ የቤተስባችን ሹፌር ኤርሚስ ነው ከእሱ ጋረ ጥሩ መቅራረብ አለን እያድረ ግን እየወደድኩት መጣው፡፡ ኤርሚ አሪፍ ልጅ ነው፤ መቀራረባችን በጣም እየጠነከረ ሄዶ በአንድ አጋጣሚ ክብረ ንጽህናዬን አሳልፌ ሰጠሁት፡፡ ግንኙነታችን አባቴ ጆሮ ደረሰና ኤርሚ ከስራ ተባረረ፡፡ ሲርቀኝ ይበልጥ እያፈቀርኩት መጣው፡፡ ከቤተሰቤቤት ወጥቼ ከሱ ጋር እንድኖር ጠይቆኛል እኔም ፍላጎቴ ይሄ ነው አባቴ ደሞ ይሄን ከሰማ ይገድለኛል፡፡ መንታ መንገድ ላይ ቆሜያለው፡፡ ከቤተሰቤ ወይስ ከኤርሚ ልሁን? እባካቹ ምክራቹን ለግሱኝ፡፡
Posted on: Fri, 09 Aug 2013 18:03:41 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015