ምን ብዬ እንደምጀምር አላውቅም ግን - TopicsExpress



          

ምን ብዬ እንደምጀምር አላውቅም ግን የምር ከፍቶኛል፤ በገዛ ሀገሬም መፃተኝነት ተሰምቶኛል፡፡ እብዶቹ የሳውዲ ሰዎች በወንድምና እህቶቻችን ላይ እየፈፀሙ ያሉትን አረመኔያዊ ድርጊት ለማውገዝ በመሰባሰባችን ብቻ የኢትዮጵያን ፖሊሶች ከእብዶቹ ሳውዲዎች ያልተናነሰ ግፍ ፈፅማብናል፡፡ ፖሊሶች ያለርህራሄ የቅርብ ቤተሰቦቻቸው በሳውዲ ጉዳት የደረሰባቸውን ሴቶች ሳይቀር በቆመጥ ሲደበድቡ ከማየት በላይ ምን ሊያም ይችላል? የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የሆኑት ይድነቃቸው ከበደ እና ጌታነህ ባልቻ እግር እግራቸውን በከስክስ እየተመቱም መፈክር በማሰማታቸው አድናቆት ሊቸራቸው ይገባል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ቁጥራቸው ከ50 በላይ የሆኑ የሰልፉ ተሳታፊዎች ግሎባል ሆቴል ጀርባ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው፡፡ እኔበበኩሌ ላልተወሰነ ጊዜ “ፖሊስ የህዝ ብ ነው” የሚለውን ለበጣ ለመስማት አልፈልግም የወያኔ አጎብዳጅ ናቸውና፡፡
Posted on: Fri, 15 Nov 2013 10:31:34 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015