ሠላም የ ልብ ወለድ ተከታታዮች ዛሬ - TopicsExpress



          

ሠላም የ ልብ ወለድ ተከታታዮች ዛሬ ስለ ጨርቆስ ልጆች ልቀልድ ነው ጨርቆሶች ታዲያ እንዳትቀየሙኝ ስለ ጨርቆስ ልጆች ከሰማሁት ውስጥ..... አንድ የጨርቆስ ሰፈር ልጅ እስኮላር ሺፕ አግኝቶ የነገዉ ሰዉ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይገባል :: የእንግሊዝኛ መምህራቸዉ በየተራ እያስነሳ ጥያቄ ይጠይቃቸዋል :: ጥያቄዉም የምነግራችሁን ቃል ተቃራኒ (Antonym) ትናገራላችሁ የሚል ሲሆን :- Fat ለሚለዉ አንዱ በፍጥነት thin ብሎ መለሰ ይሄኔ የጨርቆስ ልጅ በጣም ተገረመ እንዴት በዚህ ፍጥነት ሊመልስ ቻለ ? ብሎ ራሱን ጠየቀ :: አሁንም መምህሩ ሁሉም ተማሪዎች እስከሚመልሱ ጥያቄዉን ቀጥሉዋል :: Black ሲል መምህሩ ሌላዉ ተማሪ በፍጥነት White ብሎ ይመልሳል :: ..... መምህሩም ጥያቄዉን በመቀጠል Short ሲል አንገቱን ደፍቶ ተሸማቆ የነበረዉ የጨርቆስ ልጅ በጣም የሚያዉቀዉ ጥያቄ ስለመጣለት በደስታና በፊጥነት በመነሳት አዳር ብሎ መለሰ :: ሌላው ሰፈር ውስት ሰርግ ላይ ሃይ ሎጋ ሃይ ሎጋየሆ ሲጨፈር፣ ጨርቆስ ውስጥ ግን ቤቶቹ ጠባብ ስለሆኑ ሰለሜ ሰለሜ ነው አሉ የሚጨፈረው… ሌላው ጨርቆሶች የነጭ ጤፍ እንጀራ የሚበሉት ልክ እንደወጥ ጥቁር እንጀራ ላይ ተደርጎ ለአዲስ አመት በአል ነው ሲባል ሰምቻለሁ :: ባያስቅም ሳቁ በተረፈ የሚያስቀዉን አንዳንድ በሉ ሰላም
Posted on: Fri, 08 Nov 2013 20:31:42 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015