##ሰባት ነገሮችን አይተህ ሰባት ነገሮችን - TopicsExpress



          

##ሰባት ነገሮችን አይተህ ሰባት ነገሮችን ፈፅም########## 1 ሁሉም ሰው በሕይወት ዘመኑ ጎደኞች ቢኖሩትም ቀብር ሲገባ እንደሚተውት አይተህ መልካም ተግባርን ጎደኛ አድርግ። መልካም ሥራህ እስከመቼውም አይለይህምና። 2 "ነፍሱንም ከስሜቱ የከለከለ በእርግጥ ጀነት መቀመጫው ናት" የሚለውን የአላህ ቃል አይተህ ስሜትህን በአላህ መንገድ ምራት። ስሜትህ በመጥፎ እንጂ በጥሩ አታዝህምና። 3 "አላህ ዘንድ በላጩ አላህን ይበልጥ የሚፈራው ነው" የሚለውን የአላህ ቃል አይተህ አላህ ዘንድ ቦታ እንዲኖርህ ነፍስህን የአላህን ፍራቻ አስለምዳት። 4 "እኛ አኗኗራቸውን ከፋፈልነው (በሀብት ለያየነው)" የሚለውን የአላህን ቃል አይተህ ያንተም አላህ የወሰነልህ ብቻ መሆኑን አውቀህ ምቀኝነትን ራቅ። 5 "በእርግጥ ሸይጣን የናንተ ግልፅ ጥላት ነው" የሚለውን የአላህ ቃል አይተህ ከሰዎች ጋር መናቆርህን ትተህ ጠላትህን ሸይጣን ብቻ አድርገው። 6 "መሬት ላይ ምንም ተንቀሳቃሺ (ሕይወት ያለው) ነገር የለም፣ የሱ ሲሳይ (ሪዝቅ) አላህ ጋር ቢሆን እንጂ" የሚለውን የአላህ ቃል አይተህ አንተ አላህ ጋር ያለህን አላህ ራሱ እንደሚሰጥህ አረጋግጠህ እሱ አንተ ላይ ያለውን አደራ (የዲን ህግጋት) ፈፅም። 7 "በአሸናፊውና በመሓሪው (ጌታህ) ተመካ" የሚለውን የአላህ ቃል አይተህ መመኪያህን አላህ ብቻ አድርገው። islam onlin
Posted on: Sat, 14 Sep 2013 16:12:48 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015