ቀጣዩ የጦስ ዶሮ ማን ይሁን?ሰዎቹ - TopicsExpress



          

ቀጣዩ የጦስ ዶሮ ማን ይሁን?ሰዎቹ በደነገጡ ቁጥር እያሉ መለቃቀሙ እስከ መቼ ድረስ ይቀጥል ይሁን?....ማንም የሚያውቀው የለም።ከፈጣሪ በቀር። አንድ የፈረንጅ ሙዚቃ በኮምፒተር እየሰማሁ ነው ዘፈኙን አላውቀውም።።ለወትሮ ለሙዚቃ እምብዛም ነበርኩ። ይህን ዘፈን ግን አንድ ወዳጄ ነው ካልሰማህ ብሎ በኮምፒውተሬ ላይ የጫነው። እናም ትኩረቴን በጣም ሳበው። በጣም የዘፈኑ ርዕስ jailer (አሳሪው>>ይሰኛል።ዘፈኑ ደግሞ:- i m in chains, youre in chains too i wear uniforem and you wear uniforms too i am a prisoner.youre aprisoner too, Mr. jailer.oh i have fears,you have fear too i will die but yourself you die too im talking to you jailer. stop calling me a prisoner Let he who is without sin be the first to cast the ston You suppress all my strategy You oppress on every part of me What you dont know youre a victim too,Mr. jailer (እኔ ታስሬአለሁ፤ አንተም ይበልጥ ታስረሃል የእስረኛ ልብስ ለብሻለሁ፣ አንተም ለብሰሃል እስረኛ ነኝ፣ አቶ አሳሪ ፣አንም እኮ ታስረሃል። ፈርቻለሁ፤ ይበልጥ አንተም ፈርተሃል እሞታለሁ፤ አንተም ወደ ሞት እያዘገምክ ነው አሳሪ ሆይ:- ነግሬሀለው እኔን እስረኛ ብሎ መጥራትህን አቁም ጌታም ያለው ሀጥያት የሌለባት በመጀመሪያው ድንጋይ ይውገራት ነውና እቅዴን ሁሉ አታጨናገፍ ሁለመናዬ እያፈንከው ነው። አቶ አሳሪ አልገባህም እንጂ አንተም የዚህ ሰለባ እየሁንክ ነው።) ከሞላ ጎደል የዘፈኑ ግጥም ወደ ፌደራል ቋንቋ ሲመለስ ይሄን ይመስላል። መቼም ዘፈኑን ሙሉውን ፈልጋቹ ብታዳምጡት እና እንደ ጥጃ እየጎተተ ለሚያስሩን ወንድሞቻችን ብትጋብዟቸው ቢያንስ ድርጊታቸውን ቆም ብለው ደግመው እንዲያስቡበት ይረዳቸው ይሆናል። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
Posted on: Tue, 28 Oct 2014 20:56:46 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015