ወይ ተባበሩ አሊያም ተሰባበሩ.... አንድ - TopicsExpress



          

ወይ ተባበሩ አሊያም ተሰባበሩ.... አንድ እንጨት ብቻውን አይነድም!!! ይህ አባባል ከቀድሞው ጊዜ ጀምሮ ተቃዋሚ ናቸው ለሚባሉ ዚግዛግ ድርጅቶች እና ግለሰቦች አየር በአየር በጥቅም ላይ የዋለች ጥቅስ አይሏት ምክር; አረፍተ ነገር አይሏት የፖለቲካ ምቀኝነት እኔም ዛሬ አነሳኋት:: እንዲህ አይሏት እንዲህ ..ያልኩት ይህን ስትነግራቸው ተቃዋሚ ነን ባዮች ጆሮዋቸው ለመስማት ያዳግተዋል:: #millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ #Blueparty ወይ ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ እያልናቸው እስካሁን ባረጀ ፖለቲካ ሊታገሉ እና ሊያታግሉ የሚዳዳቸውን እነ በየነ ጴጥሮስን አይመለከትም :: ለምን ያመጡት ወይንም የፈየዱት ነገር የለምና ተሰባብረው ቁጭ ብለዋል::ስለዚ መልካሙን እየተመኙ ሳይጃጁ የፖለቲካ ፈውስ እንዲያገኙ እንጸልይላቸዋለን ወደ ሌኒን :: አዎ ይህች እስከዛሬ ምንነቷ ያለየላት ቃላት ለመጠቀም የፈለኩት እየተዋወቁ ወደ ወያኔ ያሾሉትን ጥርሳቸውን እርስ በእርስ እንዳይነካከሱበት ለፈራሁላቸው ለአንድነት እና ለሰማያዊ ፓርቲ ነው:: ትንሽ አንድነት ፓርቲ አዛውንቶቹ ፖለቲካውን እያወላገዱት ቢሆንም ወጣቶቹ መልካም ጅማሮ አላቸው ድጋፋችንን እየሰጠን ሲሆን ሰማያዊ ፓርቲም ገና በፖለቲካ ምድጃ ላይ ከመጣዱ ጉዞውን በመልካም እየሄደ ያለ ነበልባል ሰራዊታችን በመሆኑ ሁለቱንም እናከብራለን::አዎ ዲያስፖራው ያከብራቹዋል::ያው በመኖሪያ ፍቃዱ ላይ እክል የማያመጣ ትግል እንድትታገሉለት ቢፈልግም እንደኔ ግን ከፍ ብለችሁ እና ገናችሁ ይህንን አምባገነን መንግስት አስወግዳችሁ ለሃገራችን እንድታበቁን እንጠይቃለን:: አንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲ ወቅታዊውን ሁኔታ አገናዝበው በጋራ የሚሰሩበት ጊዜ መሆኑን ለመናገር እወዳለሁ:: እንደእኔ ተዋሃዱ ወይንም ተመሳሳይ የሆነጥያቄ ሳይሆን ለመናገር የወደድኩት በአሁን ሰኣት በሁለቱም ፓርቲዎች የተጀመረው የነጻነት እንቅስቃሴ በአንድ ወጥ በሆነ መልኩ በጋራ መካሄድ አለበት የሚል ምክራዊ አቋም አለኝ:: ሰማያዊ ፓርቲ የቀደደውን አንድነት አሰፋው እየተባለ ባለበት በዚህን ወቅት የጋራ የሆነ አገራዊ የነጻነት አጀንዳ ተይዞ ትግሉ መለኮስ አለበት:: ገና ሊለኮስ ክብሪቱ እና ማንደጃው ከነማገዶው የተዘጋጀውን የሃገር ቤት ትግል በጋራ ሆኖ ለኳኩሶ ማንደድ ግዴታ አለባችሁ:: ይህ ህዝብም አንድ አድርጎ የሚያቀናጀው መሪ ድርጅት ነው እንጂ ያጣው ሌላ ወኔ አላጣም:: መድረክ እያለ ራሱን የካበው ያረጁ የፈጁ ፖለቲከኞችን በጉያው የሚያባብለው ፓርቲ በመንገድ ግንባታ ሰበብ ወያኔ ከጨዋታው ውጪ አድርጎታል:: ውዶቼ ሰማያዊ ፓርቲ እና አንድነት ይህንን ለየብቻ ጎራ እየተለየ የሚጠራው ሰልፍ ነገ የፖለቲካ ግራ መጋባት በህዝቡ ላይ እንዳይፈጥር በጋራ ሆናቹ ተነጋግራችሁ በጋራ የተቃውሞ ሰልፉን ምሩት ካልሆነ የናንተ ሃራባና ቆቦ ሆኖ የትግል ጥሪ ማቅረብ ተባባሪውን ህዝብ መሃል ሰፋሪ አድርጎ ለወያኔ ሴራ መንገድ ይከፍታል:: ለየብቻ የምታደርጉት ጥረት መንገድ ቢይዝም አይሳካም አንድነት ሃይል ስለሆነ በጀመራችሁት ዘመቻ ላይ አንድ ሁኑልን::ራሳችንን ነጻ የምናወጣው እና የሃገራችንን እጣ ፋንታ የምንወስነው እናንተ ስትስማሙ የሚሊዮኖች ድምጽ የሚስተጋባው እናንተ በጋራ ስትሰሩ ሲሆን አንድ እንጨት ብቻውን ስለማይነድ እባካችሁ በነጻነት ጥያቄው ላይ ተባበሩ ሰልፉንም ስብሰባውንም አንድ አድርጉት መርሃ ግብራችሁን ሳይሆን ህዝቡን አንድ አድርጉት :: ካልሆነ የፖለቲካ መደናበር ስለሚፈጠር ትሰባበራላችሁ::
Posted on: Sun, 21 Jul 2013 02:13:09 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015