ወደ ኋላ ሶስት ወር ልመልሳችሁ፡፡ - TopicsExpress



          

ወደ ኋላ ሶስት ወር ልመልሳችሁ፡፡ በየካቲት ወር በዋሽንግተን ዲሲ ‘የታሰሩት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት’ እንዲፈቱ የሚጠይቅ አንድ መድረክ ተዘጋጀ፡፡ ግብፃዊ አሜሪካዊው ሼክ ሻኪር በዚህ መድረክ ተገኝተው እንዲህ አሉ፡፡ “መልካሙን ዜና ልንገራችሁ፡፡ በቃ አሸባሪ ብለው ፈርጀውናል፡፡ ቤታችሁ ብትቀመጡም፤ ቴሌቪዥን እያያችሁ ብትሆኑም፤ ቡና እየጠጣችሁ ብትሆኑም፤ ተኝታችሁ ብትሆኑም ወይም ደግሞ ከልጆቻችሁ ጋር እየተጫወታችሁ ብትሆኑ አሸባሪ ናችሁ፡፡ ምክንያቱም እናንተ ሙስሊም ናችሁና፡፡” ወደ ኋላ ሶስት ቀናት ልመልሳችሁ፡፡ በአዲስ አበባ ‘የታሰሩት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት’ እንዲፈቱ የሚጠይቅ አንድ የተቃውሞ ሰልፍ ተዘጋጀ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢትዮጵያዊው ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት በዚህ መድረክ ተገኝተው ቃል በቃል እንዲህ አሉ፡፡ “እዚህ የተሰባሰባችሁት ብዙዎቻችሁ ወጣቶችና ጋዜጠኞች ናችሁ፡፡ እዚህ ሀገር ደግሞ ለናንተ የተሰጣችሁን ስም ታውቁታላችሁ፡፡ በሱ ስም ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ፡፡ አሸባሪዎች እንደምን ዋላችሁ፡፡” kebedekassa.blogspot/2013/06/vs.html
Posted on: Fri, 07 Jun 2013 14:38:41 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015