የጀሃዳዊ ሃራካት ሲሰራ ቶርች ሲፈጽሙ - TopicsExpress



          

የጀሃዳዊ ሃራካት ሲሰራ ቶርች ሲፈጽሙ የነበሩት ሶስት ደህንነቶች ወደ መቀሌ ሲቀየሩ ሁለት ማእከላዊ ጣውላ እስር ቤት ታስረው ይገኛሉ::#Ethiopia #EthioMuslims በማዕከላዊ እስር ቤት ኮሚቴዎቻችንን እና ሌሎች ሙስሊሞችን ሲደበድቡ እና ሲያሰቃዩ የነበሩ ሁለት የደህንነት አባላት መታሰራቸው ተሰማ::በማዕከላዊ እስር ቤት ከዚህ ቀደም ውድ ኮሚቴዎቻችንን እና ሌሎች ሙስሊሞችን በምርመራ ወቅት ከፍተኛ የሆነ ድብደባ እና ስቃይ ሲያደርሱ የነበሩ ሁለት የደህንነት አባላት እዛው ማዕከላዊ እስር ቤት መታሰራቸውን የውስጥ ምንጮች አስታወቁ፡፡ሁለቱ ደህንነቶች የታሰሩት በተደረገባቸው ግምገማ መሆኑ ታውቋል፡፡ አቶ መርሻ የተባለው እና ሌላኛው ስሙ ለጊዜው ያልተተቀሰው የደህንነት አባል ለእስራት ያበቃቸው ግምገማ ምን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም፡፡ ሁለቱ ደህንነቶች በታሰሩበት ወቅት በቅድሚያ በማዕከላዊ እስር ቤት ሸራተን ተብሎ በሚጠራው ክፍል ሲሆን በክፍሉ ታስረው የሚገኙትን እና ሲደበድቧቸው የነበሩትን ታሳሪዎች ተፀፅተው ይቅርታ መጠየቃቸውን የውስጥ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ሁለቱ ታሳሪዎች በአሁኑ ወቅት ከሸራተን ወደ ጣውላ ክፍል መቀየራቸው ታውቋል፡:ከነዚህ ሁለት የደህንነት አባላት በተጨማሪም 3 የደህንነት አባላቶች በተደረገባቸው ግምገማ ወደ መቀሌ እንዲዘዋወሩ እንደተወሰነባቸው የውስጥ ምንጮች ጨምረው ገልፀዋል፡፡
Posted on: Sun, 29 Sep 2013 13:34:18 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015