ያለፈው ዓመት ይህን ይመስል - TopicsExpress



          

ያለፈው ዓመት ይህን ይመስል ነበር በእስራኤል የሚገኙ ኢትዮጵያኖች እንደሚታወቀው ከአመጣጣቸው ጀምሮ እስካሁን ድረስ ብዙ ውጣ ውረድ ያሳለፉ ሲሆን እነደው እንዳጋጣሚም ይሁን ልክ እንደ እሳተ ገሞራ ውስጥ ለውሰጥ ተጠንስሶና ተሟሙቆ ጊዜውንም ጠብቆ የፈነዳ ይመስላል ሁሉም ሀበሻ በተወዳደሩበት መድረክ አሸናፊነትን የተጎናፀፉት። በዚህ ባሳለፍነው ዓመት ነበር በዋና ዋና ማህበራዊ ጉዳዮች ለይም ትኩረትን ሲስቡ የታዩት። ከዚህ በፊት መቼም "ለመደሀኒት አንድ" እንዲሉ በሃገሪቷ ፓርላማ ውስጥ አንድ ሃበሻ መታየቱ አልቀረም ነበር። በዚህ ባሳለፍነው ዓመት ግን ወደ ሁለት ከፍ ብሏል። "በትልቅ ወንድም" ፕሮግራም ለይ ተሳታፊ ሆና አሸናፊ የሆነችዋ ሓበሻ ትሁኔ ሮቤል አብዛኛውን የአስራኤል ዜጋ ለቆዳ ቀለማችን ያላቸውን አመለካከት ግልፅ አድርጋ አሳይታናለች። በርግጥ በፕሮግራሙ ለይ ያሳየችው ባህሪይ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ለይ የማይታይና የሌለ ቢሆንም ዘረኝነትንና ጥላቻን ልንታገልበት የምንችለው በዚህ አይነት መልኩ ከሆነ ልብ ያለው ሸብ እላለው። በአጠቃላይ ይህ አመት በሪከርድነት ተመዝግቦ እንዳይቀር ቀጣይነት ይኖረው ዘንድ መተባበሩና መተሳሰቡ ሳይሻል አይቀርም። የአመቱ ኮከቦቻችን አነዚህ ነበሩ 1 ትሁኔ ሮቤል (Big Brogher) Israel 2 ቲቲ አያናው( Ms Israel) 3 ሃጊት እያሱ ( Idol Israel) ቀጣይነት ይኖረው ዘንድ መልካም ምኞቴን አደርሳለው!! መልካም አዲስ ዓመት!
Posted on: Tue, 03 Sep 2013 21:41:09 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015