ድምፃችን ይሰማ #Ethiopia #EthioMuslims - TopicsExpress



          

ድምፃችን ይሰማ #Ethiopia #EthioMuslims #JumaDemonstration #Ramedan የጁምዓን ተቃውሞ በማስመልከት አጭር መልዕክት ረቡእ ሐምሌ 10/2005 ሕገ መንግስታዊ መብታችን ይከበር ዘንድ አደባባይ በመውጣት በአገር አቀፍ ደረጃ የተቃውሞ ትግል ማድረግ ከጀመርንበት ከጥቅምት 2004 ጀምሮ ቁጥራቸው ከመቶ በላይ የሚልቁ የጁምዓ ተቃውሞዎችን አድርገናል፡፡ የእንቅስቃያችን አካል የሆነው የጁምዓ የተቃውሞ መድረክ በርካቶችን ባስደመመ ሁኔታ እንደቀጠለ ይገኛል፡፡ የተቃውሞውን ድምቀትና ወጥነት እንዲሁም ስርዓት ከማስጠበቅ አኳያ ህዝቡ ለሚተላለፉት ትእዛዝ ቀጥተኛ የሆነ ታዛዥነት ማሳየት መቻሉ ከአስደማሚ ገፅታዎቹ ቀዳሚውን ድርሻ ይይዛል፡፡ ስርዓት የተሞላበት የተቃውሞ ውሎ ከምንም በላይ እጅግ አስፈላጊ መሆኑንም ትምህርት ያገኘንበት አጋጣሚ ነው፡፡ የዚህ የጁምዓ አገር አቀፍ የተቃውሞ ውሎ አዘጋጅም ሆነ አስተባባሪ በግልፅ በሚታይ መልኩ ራሱ ሕዝቡ ነው፡፡ ዲሲፕሊን ማስጠበቅ በተለይም በዕለቱ የተዘጋጀውን የተቃውሞ መርሐ ግብር ሳያዛቡ ተግባራዊ ማድረግ የሚከተሉት ጠቀሜታዎች ይኖሩታል፡፡ 1. አጋጣሚውን በመጠቀም ግርግርና ረብሻ ለመፍጠር የተሰገሰጉትን ኃይላት ተንኮል ማክሸፍ ያስችላል፣ 2. ሠላማዊነታችን ዋና መገለጫ መሆኑንና መንግስት እንደሚለው አሸባሪና ጸረ-ሰላም አለመሆናችንን ለሌላው ኢትዮጵያዊ ማሳየት ይቻለናል፣ 3. ይዘነው የመጣነውን መልዕክታችንን ለመንግስትም ሆነ ለሌላው ወገን ባግባቡ ማድረስ ያስችለናል፣ 4. ሰዓታችንን በግባቡና ውጤታማ በሆነ መልኩ መጠቀም ያስችለናል፣ 5. የጥቂት ወንድሞቻችን፣ እህቶቻችንን እንዲሁም ሕጻናትን የተለየ ተጋላጭነት እንድንከላከል ያስችለናል፣ 6. በቦታው የሚተላለፍ ልዩ መልዕክት ካለ ሁላችንም እንድንሰማውና እንድንተገብረው ያስችለናል፣ 7. ከምንም በላይ ትግሉ ራሳችን ያዘጋጀነው፣ ራሳችን የምናስተባብረው እና የምንቆጣጠረውና ሕዝባዊነቱን ለማሳየት ያስችለናል፣ 8. በዲሲፕሊን የተሞላንና ታዛዥነትን በተግባር የምናረጋግጥ መሆናችንን እናሳይበታለን … ወዘተ ከዚህ ቀደም በነበሩት አንዳንድ የተቃውሞ ጊዜያቶች ያጋጠሙንን ፈታኝ ክስተቶች መከላከል የቻልነው የአላህ ፈቃድ ሆኖ የተቃውሞው ስርዓቱ በተዘጋጀለት ገዥ መርሐ ግብር እንዲመራ ለማድረግ ያደረግነው ሁለንተናዊ ርብርብና ትጋት ነው፡፡ ይህም በሚዘጋጀው ወጥ የሆነ መርሐ ግብር መሠረት የዕለቱን የጁምዓ ተቃውሞ መተግበር፣ ማስተግበር እና ማስተባበር የሚያስገኘውን ፋይዳ ጠንቅቀን እንድረዳ አስችሎናል፡፡ ለምሳሌ የሚባሉ መፈክሮች በዕለቱ የተዘጋጁት ብቻ መሆናቸው፣ የምናሳያቸው ምልክቶች በዕለቱ የተወሰኑት ብቻ መሆናቸው፣ ሁላችንም ተቃውሞ ተጀምሮ እስከሚያልቅ ድረስ ባለንበት ቦታ በመቆም ወይም በመቀመጥ ብቻ መቆየት መቻላችን ሁሌም ትኩረት ልንሰጠው የሚገባን ጉዳይ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህ ታሪካዊ የተቃውሞ ስርዓትና ስልት በታሪክ የወርቅ ብዕር ራሱን ማስፈር እንደጀመረው ሁሉ ይኸው ተጠናክሮ ይቀጥላል ኢንሻ አላህ፡፡ በዚህ ሳምንትም የጁምዓ ተቃውሟችን በአገር አቀፍ ደረጃ የሚቀጥል ሲሆን በተሻለ ድምቀት መከናወን ይችል ዘንድ ሁላችንም ከወዲሁ ቅስቀሳ በማድረግ፣ በብዛት በመገኘትና ወጥነት ባለው መንገድ በመፈፀም ሃላፊነታችንን እንወጣ፡፡ አላህ መልካሙን ይግጠመን፡፡ በአላህ ፈቃድ የተቃውሞው መርሐግብር ነገ ይፋ ይሆናል፡፡ አላሁ አክበር!
Posted on: Thu, 18 Jul 2013 01:04:43 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015