የሙስሊሙ ዓለም የነፃነት ትግል እና - TopicsExpress



          

የሙስሊሙ ዓለም የነፃነት ትግል እና አብዮት በቅርቡ በአረቡ ዓለም የተነሳው አብዮት ህዝቡ ለታገለለት አላማ እና ፍላጎት ሙሉ በሙሉ አልዋለም ማለት ይቻላል። በዚህ አጭር ፁሁፍ ውስጥ የነዚህን አብዮቶች የተነሱለት አላማና መንስኤው እንዲሁም የጋጠሙተን እንቅፋቶች ለመዳሰስ እንሞክራለን። በግብፅ ለውጥ የፈለገው ህዝብ የንጉሥ ፋሩቅን ዘውዳዊ አጋዛዝ ገርስሶ በኢማም መሐመድ አብዱላ እና ሼክ ጀማል አል -ዲን-አል-አፍጋኒ መሪነት እስልምናን ማእከል ያደረገ መንግስት የመመስረት ፍላጎቱ በ1952 ከጦር ኃይሉ በመጡት ሰልጣኑን በመያዝ እስለመናን ወዳ ጎን ገሸሽ በማድረግና የሽእርያ ሕግ ሽረው ከፈረንሳይ እና እንግሊዝ ቀድተው ያመጡትን ሕግ አወጁ :: በ2011 የግብፅ ሕዝብ እንደገና አምባገኑን የሆስኒ ሙባረክን ሰርዓት ከሰልጣን ካወረደ በሁላ ለመጀመሪያ ጊዜ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የመረጠወን ፕሬዝዳንት በሾመበት ማግስት ፍፁም ኢ-ዴሞክረሳዊ በሆነ መንገድ የምእራብዊያን “የማደጎ ልጅ” በሆነው የግብፅ ጦር ኃይል ባካሄዳው መፈንቅለ-መንግስት ፕ/ት ሙሐመድ ሙርሲን ወህኒ ወርውረው የህዝቡን አዲስ የፈነጠቀውን ተስፋ ያጨለሙበት ክስተት የቅርብ ጊዜ ትወስታ ነው። በየመን ኡለማዎች፣ዳኞችና እነ አል-ዙበይር, ኢብን-አል-ኑእማን, አል-ኩብሲ በመሳሰሉ ሙሁራን እና ሌሎችም መሪነት በ1962 በኢማሜቱ ላይ በቀሰቀሱት አብዮት እስላማዊ ተቁአማትን ማቁቁም ቢቺሉም የጃማል አብዱልናስር ተከታይ በሆነው አብዱላህ አል-ሳላል ከጦር ኃይሉ ጋር በማበር አብዮቱን አኮላሹት:: የየመንን ሕዝብ በእስላማዊ ሕግ የመመራት ሕልም አጨናግፋው እንደ ግብፁ ሁሉ ከዚህም ከዛም ያመጡት ሕግ ህዝቡ ላይ በህይል ጫኑበት። የዚህ እኩይ ተግባር መዘዝ እስካለንበት ቀን ድረስ ሀገሪቷን ከማትወጣው መስቅልቅል ዶሏታል። እስላማዊ እሳቤና መርህ አንግበው የተነሱት በኡላማዎች የሚመራው የአልጄሪያ ወርቅ ትውልድ ታሪካዊውን የፅረ-ቅኝ ግዛት ትግል አካሂዶ የፈረንሳይን አጋዛዝ ካበቃና አልጄሪያ ነፃ ከወጣች በሃላ የሶሺያሊስት ርዕዮተ ዓለምን በሚያቀነቅኑና ‘’westernized’’ በሆኑ ሰልጣኑን በተቆናተጡት ቡድኖች የተነሱለት አብዮት አላማ ሊጨናገፍ በቅቷል። በሱዳንና በሊቢያ ሙስሊሞች ላይ የደረሰው ክዚህ የተለየ አልነበረም. ሱዳን ላይ በማሀዲዎች መሪናት ከእንግሊዞች ጋር እና ሊቢያ ላይ በጀግናው ዑመር አል-ሙክታር መሪነት ከፋሺስት ጣልያን ጋር ያረጉትን የጀግነነት ገድል ማውሳት ይቻላል። ኢራቅና ሶርያ መቶ ፐርሰንት ሙስሊሞች ናቸው.ላዚህም ነው በእስልምና ጥላ ስር ተደራጅታው በእንግሊዝና ፈረንሳይ ላይ የፀረ-ባርነት ትግላቻወን ያካሄዱትና ወድ ህዋታቸውን የሰዉት. የሁንና ባዝ ፓርቲና ተከታዮቹ አላህ አምሳያ አንደሌላው ሁሉ የባዝ ፍልስፍናቸውን ሰውን አስከማስመለክ ደርሰዋል። ከአላህ ሕግ በላይ ሌላ ሕግ የለም, የህጎች ሁሉ ባላጭ የአላህ ሕግ ነው . ላዚህም እውነት ደሞ የሚመስክሩት ሙስሊሞች ብቻ ሳይሆኑ የምራባውያን ታዋቂ የታሪክ ሙሁራንና ጠበብት ጭመር ናቸው. ለአብነት ያህል የ “ The Saudis and the Islamic Solution,” መፅሐፍ ፃፊ ጃላል ኪሽክ ሰለ እስላም ትክክለኝት ግልፅ በሆነ መልኩ በማስረጃ አስደግፎ ፅፏል። የኦስትርያው የታሪክ ፃፊ ሙሐመድ አሳድ የፃፋው “The Road to Mecca” እና ለሎቼን መጥቃስ ይቻላል. ይህ እውነታ ነው ሀቅ ነው። የዚህ ሁሉ ትግል አላማ አንድና አንድ ብቻ ነው፣” የአላህ ሕግ” የሙስሊሞች ሀገር በቁራንና ሱና መመራት አለባቻው። There is no god other than God, and Muhammad is His Messenger;” የፁፋችን መልእክት እና መቁዋጫ ነው። ዋሳላሙአሌይኩም ወራህመቱላ ወበረካቱሁ
Posted on: Sun, 27 Oct 2013 19:48:24 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015