የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibrets views - TopicsExpress



          

የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibrets views ADVERTISMENT ለቤተ መጻሕፍትዎ ልዩ ልዩ ከመንፈሳዊዉ ዓለም ወግ የጉዞ ማስታወሻ ጥናታዊ ጽሑፎች Thursday, October 17, 2013 አንድ ከሰዓት በመንበረ ፓትርያርክ click here for pdf የመንበረ ፓትርያርክ 32ኛው ጉባኤ የረቡዕ ዕለት ከሰዓት ውሎ ካለፉት የተለየ ነበር፡፡ ዋና አጀንዳው ‹መቻቻልን› የተመለከተ ሲሆን አቅራቢዎቹም ከፌዴራል ጉዳዮች የተወከሉ አካላት መሆናቸውን በዕለቱ የመርሐ ግብር ዝርዝር ላይ ተገልጧል፡፡ ከሰኞ ጀምሮ ይቀርብ በነበረው የአህጉረ ስብከት ሪፖርቶች ላይ የመብት ጥሰትና ሥልጣንን ለግል ሃይማኖት ማስፋፊያ የመጠቀም አዝማሚያዎች መኖራቸውን፣ በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠው እምነትን የመያዝ፣ የማስፋፋትና የአምልኮ ቦታ የማግኘት መብት እየተጣሰ መሆኑን የሚገልጡ ዘገባዎች ይሰሙ ነበር፡፡ በትናንትናው የከሰዓት ውሎ ስለ መቻቻል ገለጣ ከተሰጠ በኋላ ብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳትና የጉባኤው ተሰብሳቢዎች የየአካባቢያቸውን ችግሮች በዝርዝር ነበር ያነሷቸው፡፡ ‹‹መቻቻል እስከ ምን ድረስ ነው›› ብለው ነበር ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ የጠየቁት፡፡ ‹‹አሁን በምዕራብ ወለጋ ያለው ሁኔታ መንግሥት በአገሩ ያለ ይመስላል ወይ? ሰው እግሩን እሳት እየበላው ቻል ይባላል እንዴ? እንድንቻቻል አድርጉን፣ እንችላለን›› ነበር ያሉት፡፡ የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሄኖክ ‹በነጆ ወረዳ በሕጋዊ መንገድ ተሠርቶ የነበረው ቤተ ክርስቲያን በአካባቢው ባለ ሥልጣናት ተጽዕኖ እንዲፈርስ መደረጉን፣ ለምን ታፈርሳላችሁ ብለው ድርጊቱን የተቃወሙ ስድሳ ምእመናን መታሠራቸውን›› በኀዘን ነበር የገለጡት፡፡ አያይዘውም ‹‹በባኮ ወረዳ የተመደቡ አንድ ካህን እያረሱ እያሉ የአካባቢው ባለ ሥልጣናት መጡ፤ ካህኑን በሰደፍ እየደበደቡ ‹ከዚህ ሀገር ልቀቁ፣ ይህ የነፍጠኛ መኖሪያ አይደለም› እያሉ አሰቃዩዋቸው፡፡ ካህኑን ሲደበድቧቸው አንበርክከው፣ ለ15 ደቂቃ አተኩረው ፀሐይዋን እንዲያዩ እያስገደዱ ነበር፡፡ ድብደባውን ሰምተው የወጡት ባለቤታቸው በድንጋጤ ታመው ከጥቂት ቀናት በኋላ ሕይወታቸው አለፈ›› ‹‹በሰንበትና በቅዱስ ሚካኤል ቀን ምእመናን ሊያስቀድሱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄዱ ‹ለቅዳሴ ካህናቱ ይበቃሉ፤ እናንተ ውጡ›› እየተባሉ እንዳያስቀድሱ ይደረጋሉ፡፡ ከእኛ ቤተ ክርስቲያን 70 ሜትር ርቀት ላይ ሆን ተብሎ እርስ በርስ ለማጋጨት ለፕሮቴስታንቶች የጸሎት ቦታ ተሰጠ፡፡ ለምን ታጨቃጭቁናላችሁ፤ ይህ ቦታ ለእነርሱ አይሆንም ብሎ በመከራከሩ አንድ ዲያቆን ተደብድቦ ሞተ፡፡ የሕክምና ውጤቱም ሆን ተብሎ በወባ በሽታ ሞተ ተብሎ ተሠራ፡፡ ለሁለት ዓመት ያህል ተከራክረን አሁን ቦታው ለእኛ ተወሰነ፡፡ ጊምቢና መንዲ ላይ የምእመናን ልጆች ትምህርት ቤት ውስጥ በፖሊስ ማተባችሁን በጥሱ እየተባሉ ነው፡፡ ለምን ስንላቸው ከላይ የወረደ መመሪያ አለ ይሉናል፡፡›› ቀጥለው የሀገረ ስብከታቸውን ችግር ያቀረቡት የጋሞጎፋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤልያስ ነበሩ፡፡ ‹‹በጋሞ ጎፋ መቱ ወረዳ፣ ዋጁ ኡቆ ላይ የመስቀል ማክበሪያ ቦታችን ለሱቅ መሥሪያ ቦታ ተሰጠ፡፡ አቤት ብንል የሚሰማን በማጣታችን ዘንድሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መስቀል ሳናከብር ዋልን፡፡ ሀገሪቱ በችግር ላይ በነበረች ጊዜ እንኳን መስቀል ሳይከበር ቀርቶ አያውቅም ነበር፡፡ የቤተ ክርስቲያን የይዞታ ቦታ ለመንግሥት እየተሰጠ ነው፡፡ በአቡነ ጳውሎስ ዘመን በቅዱስነታቸው በኩል ለክልሉ ደብዳቤ ጻፍን፡፡ ክልሉ ወሰነልን፡፡ ነገር ግን እስካሁን አልተረከብንም፡፡›› ቀጥለው ሃሳባቸውን የሰጡት የባሰ ካልመጣ በቀር ድምጻቸው ማይሰማው ብጹዕ አቡነ ያሬድ የሶማሌ ክልል ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነበሩ፡፡ ‹‹በሶማሌ ክልል አምስት አብያተ ክርስቲያናት ብቻ ናቸው ያሉን፡፡ ምእመናኑ ብዙ ናቸው፡፡ ሲወልዱ የሚያስጠምቁበት፣ ሲያርፉ የሚቀበሩበት ቤተ ክርስቲያን እንትከል ብንል የሚሰማን አጥተናል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን የሚረዱ ምእመናን በግላቸው ጥቃት እየደረሰባቸው ነው፡፡ ለዚህ መልሳችሁ ምንድን ነው›› ብለዋል፡፡ በገለጻው ላይ ኢትዮጵያ ክርስትናን የተቀበለችው በ4ኛው መክዘ ነው የሚለውን የተቃወሙት ብጹዕ አቡነ ማርቆስ ‹‹ታሪክ ክፉም ሆነ በጎ እንደ ታሪክነቱ መተረክ አለበት፤ አቅራቢው ወንድማችን በ4ኛው መክዘ ክርስትና ገባ ያልከው ተሳስተሃል፡፡ ለመሆኑ ይህንን ለማለት ‹ላይሰንስ አለህ?› አባቱን የሚኮንን ልጅ ምን ያደርጋል? ነገሥታቱን ወቀሳችሁ፣ ቤተ ክርስቲያንን ነቀፋችሁ፤ ለመሆኑ ከማን ነው ይህቺን ሀገር የተረከባችሁት? ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የገባው ጌታ ባረገ ዓመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 8 ላይ አለ፡፡ ይህንን ዛሬ ‹ግራጁዌት አድርገው›፤ ልዑካኑ ስትመጡ ስለምትናገሩት ነገር ዕወቁ፤›› የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ እንድርያስም ‹‹በቤተ መንግሥት የወርቅ ዕቃ ብቻ አይኖርም፣ የእንጨትም፣ የድንጋይም ዕቃ አለ፡፡ በቤተ ክርስቲያንም ሁሉም ጥሩ አይሆንም፣ መጥፎም ይኖራል፡፡ ነገር ግን እስከ መጨረሻው የጸና ይድናል ብሏል፡፡ በእኔ ሀገረ ስብከት ስድስት አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፡፡ ሦስቱ በአንድ አካባቢ፣ ሦስቱ በሌላ ቦታ፡፡ ይህንን ለክልሉ መንግሥት ብናሳውቅ አልረዱንም፡፡ የተበደለ ሰው ይጮኻል፤ ሲጮህ ደግሞ ፖለቲካ ነው ይባላል፡፡ ድሮ ያስቸገረን የንዋያተ ቅድሳት ዘረፋ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ወደ ማቃጠል ተዛውሯል፡፡ አንዱ ባለ ሥልጣን እንዲያውም ችግሩን ሳቀርብለት ተቆጣኝ፤ ብዙ ብናገር ነፋስ ስለሚወስደው እዚህ ላይ ይብቃ›› ከብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳት ቀጥሎ የተናገሩት የወላይታ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ‹‹በበዴሳ ወረዳ ያለ አንድ የሌላ እመነት ተከታይ የሆነ ዳኛ ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጋር ቄራ አንካፈልም፤ በመኪና አብረን አንሄድም› ብሎ ዐወጀ፡፡ በጋራ በመቻቻል የኖርንበትን ዕድር ሁሉ ለዩ ብሏል፡፡ ታድያ እንዴት መቻቻል ሊመጣ ይችላል፡፡›› ከጉባኤው የቀረበውን ቅሬታና ሃሳብ ያዳመጡት የፌዴራል ጉዳዮች የሥራ ኃላፊዎች የቀረቡት ቅሬታዎች በሰነድ ተደግፈው ቢደርሷቸው እነርሱም በመፍትሔው ላይ መሥራት እንደሚችሉ፤ ኢትዮጵያ የሃይማኖቶች ጉባኤም ጉዳዩ በየደረጃው ቢቀርብለት መፍታት እንደሚችል፡፡ ቅሬታዎችን እንደዚህ ባለ መድረክ ከሚሆን በየጊዜው እየተገናኙ መፍታት ቢቻል›. የሚሉ ሃሳቦችን ሠንዝረዋል፡፡ የዘንድሮው የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ በአደረጃጀቱ ውበት፣ በተሳታፊዎቹ ብዛት፣ በአህጉረ ስብከቶች ቁጥር(50 ደርሰዋል)፣ በስብሰባው ቁም ነገረኛነት ካለፉት የተለየ ነበር፡፡ እነ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ የሰበካ ጉባኤ ስብሰባ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን በብርቱ እንደ ደከሙበት ያሳያል፡፡ በየዘገባዎቹ የተሰሙትን የመብት ጥሰቶች፣ ሥልጣንን ተገን በማድረግ የሚፈጸሙ ጫናዎች፣ የአምልኮ ቦታ እጥረቶች፣ በካህናቱ ላይ የሚፈጸሙትን ግፎችና፣ የቤተ ክርስቲያንን ይዞታ የመንጠቅ ርምጃዎች ግን ሊገቱ ይገባቸዋል፡፡ ከአንዳንድ ክልሎች በቀር በብዙዎቹ የዞንና የክልል ባለ ሥልጣናት ችግሩን ተረድተው ለመፍታት እንደሚጥሩ ተገልጧል፡፡ በወረዳ ደረጃ የሚገኙት ግን ሥልጣንን ተገን በማድረግ የግል እምነታቸውን እያስፋፉ መሆኑን ያሳያል፡፡ በደቡብ ጎንደርና በምሥራቅ ጎጃም የተፈጸሙት የአብያተ ክርስቲያናትን የማቃጠል ርምጃዎች በጊዜው ተጣርተው መፍትሔ ካልተሰጣቸው ፍጻሜያቸው አያምርም፡፡ በየአካባቢው በሚገኙ ባለ ሥልጣናት የሚፈጸሙ ትንኮሳዎችም መቆም አለባቸው፡፡ ብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳቱ ‹አታስቆጡን› እያሉ ደጋግመው የተናገሩት ነገር የዋዛ አይደለም፡፡ ኃላፊነት የማይሰማቸው አካላት የሚፈጽሙት ገደብ አልባ ትንኮሳና ጫና ወዴት እያመራ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱም አደረጃጀቷንና አሠራርዋን ይበልጥ የምትፈትሽበት፣ አሁን ለገጠማት ተግዳሮት ብቁ የሚሆን አሠራና አወቃቀር የምትይዝበት፣ ችግሮችን በስብሰባ ብቻ ሳይሆን በአካባቢያዊ ውይይት፣ በሕግ መሥመርና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀራርቦ በመሥራት የምትፈታበት መንገድ ሊኖር ይገባል፡፡ ያለበለዚያ መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል የተረተው ተረት መድረሱ የማይቀር ነው፡፡ በጣልያን ጊዜ ነው አሉ፡፡ ጎንደር ላይ ጣልያን በድማሚት አንዱን ተራራ ያናውጠዋል፡፡ ተራራው ‹እድም› እያለ ይፈርሳል፡፡ አንዲት የከብት እረኛ ልጅ ፈርታ ወደ እናቷ ሄደችና ‹እማዬ ኧረ ጣልያን ተራራውን እያፈረሰው ነው›› አለቻት፡፡ እናቷም ‹‹እነ ደጃዝማች እገሌ፣ እነ ፊታውራሪ እገሌ፣ እነ ራስ እገሌ እጅ አንሰጥም ብለው እየተጋደሉ ዐለፉ፡፡ ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡›› አለቻት አሉ፡፡ Email ThisBlogThis!Share to TwitterShare to Facebook Posted by ዳንኤል ክብረት 49 comments: AnonymousOctober 17, 2013 at 1:15 PM Amlake Kidusan Yitbkat Enji lela min yibalal? Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 1:33 PM ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡ Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 1:39 PM the work of devils is still continued, it is really time to cray, pray and stand together to our church!. this is the objectives of this government, the Muslims and protestants are aiming to attack the truth( EOTC). They want their leadership to accomplish to fight our church. the Federal Affairs asking the document but they knows each and every thing happen in the church. In every direction and corner all this devils including the government are objectively working day and night to undermine the work or the contribution of EOTC for this country. why? why? why...? the people of EOTC are choosing silent? why our church leaders are strong enough to challenge the government and teach the people so as to keep his church and ask his right of living, prying and take measure on devils......... Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 1:57 PM አብያተ ክርስቲያናትን የማቃጠል ርምጃዎች በጊዜው ተጣርተው መፍትሔ ካልተሰጣቸው ፍጻሜያቸው አያምርም፡፡ Reply Birhan BihilOctober 17, 2013 at 1:58 PM ...መቼስ ዦሮ መስማት...ዓይን ማየት አይከለከል... ለሊቃውንቱ ለአባቶቻችን ያውም በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ....ስለመቻቻል፣ ስለ ክርስትና መጀመር በኢትዮትያ ሊናገሩ ከፌዴራል ጉዳዮች መጡ!...እህህህህህህ.... እስቲ ይሁን... የኦርቶዶክሱን ክርስቲያን የተማረከ ወታደር አደረጉትኮ... ለነገሩ ምን ያድርጉ በማያገባቸው እየገቡ የፈለጉትን ሲያደርጉ...ትላንትም...ዝም...ዛሬም ዝም....ነገም.... ?????? ዝም ከሆነ መልሳችን... ??????? Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 1:58 PM አባቱን የሚኮንን ልጅ ምን ያደርጋል? ነገሥታቱን ወቀሳችሁ፣ ቤተ ክርስቲያንን ነቀፋችሁ፤ ለመሆኑ ከማን ነው ይህቺን ሀገር የተረከባችሁት? Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 2:08 PM ቃለ ሕይወት ያሰማልን! እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ አሉ! ግሩም ነው! እስኪ በዚህ ይብቃንና የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በቃ ለማለት ልቦናውን ፈጣሪ ይስጠን አሜን! Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 2:09 PM mengst be ye akababi endngach aderegen yehager smetachin yaferese meselew gn yihe metfo zemen alfo betekrstianachin yemtkeberbet ken yimeta yihon? Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 2:11 PM ‹‹በሰንበትና በቅዱስ ሚካኤል ቀን ምእመናን ሊያስቀድሱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄዱ ‹ለቅዳሴ ካህናቱ ይበቃሉ፤ እናንተ ውጡ›› እየተባሉ እንዳያስቀድሱ ይደረጋሉ፡፡ ከእኛ ቤተ ክርስቲያን 70 ሜትር ርቀት ላይ ሆን ተብሎ እርስ በርስ ለማጋጨት ለፕሮቴስታንቶች የጸሎት ቦታ ተሰጠ፡፡ ለምን ታጨቃጭቁናላችሁ Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 2:25 PM ግሩም አስተያየት! እግዚአብሔር አምላክ ቤተ ክርስቲያንን ከነፎች ይጠብቅልን፡፡ ዲያቆን ዳንኤል እድሜና ጤና ይስጥልን፡፡ አሜን፡፡ Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 2:46 PM በኢትዮጵያ የሚገኙ ፕሮቴስታንት ድርጅቶች አብዛኞቹ እንደ አላማ አስቀምጠው ከሚሰሩባቸው ጉዳዮች አንዱ የመንግስትን ስልጣን መዋቅር መቆጣጠር ነው ። ይህን ደግሞ የሚናገሩት በህቡዕ ሳይሆን በየአዳራሾቻቸው በሚደረጉ ስብከቶችና እንደ መስርያ ቤቶች ራዕይ ዓላማ ግብ ተብለው ተጽፈው በሚሰቀሉ ቢል ቦርዶች ላይም ጭምር ነው። ልብ በሉ ሌሎች ባለፈው ስርአት ተጎድተናልና አሁን እኛ ስልጣኑን መያዝ አለብን ብለው በተደራጀ ሁኔታ ሲንቀሳቀሱና ፕሮቴስታንት ደግሞ ሲጨመርበት ኦርቶዶክሳውያን ምን እየተሰራ እንደሆነ መረዳት አልቻልንም። Reply akeOctober 17, 2013 at 3:05 PM HI D/DANIEL. THANKS FOR YOUR POSTS Min yishalenal endih yemeselech betekirstianachin sikatel mayet. bizu lela yalteneger bewolaita zone wust ale mihmenun masferarat. ara mela yibal lebizowch yemaytay neger ale bicha....eg/r mechereshawun yasayen. dani ameseginalew Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 3:23 PM God bless our fathers. Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 3:40 PM Egziabhaer Melkam new Bemekera kenim Mesheshegia New !!!!!! Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 4:10 PM እግዚአብሔር ይባርክህ፣ይጠብቅህ እድሜና ጤና ይስጥህ አባቶቻችን ለካ አሉ ማለት ልጀምር ይሆን Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 4:15 PM good keep going Reply kirubelOctober 17, 2013 at 4:18 PM ........ እናቷም ‹‹እነ ደጃዝማች እገሌ፣ እነ ፊታውራሪ እገሌ፣ እነ ራስ እገሌ እጅ አንሰጥም ብለው እየተጋደሉ ዐለፉ፡፡ ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡›› አለቻት አሉ፡፡ ...EG/R yerdane Reply kirubelOctober 17, 2013 at 4:18 PM እናቷም ‹‹እነ ደጃዝማች እገሌ፣ እነ ፊታውራሪ እገሌ፣ እነ ራስ እገሌ እጅ አንሰጥም ብለው እየተጋደሉ ዐለፉ፡፡ ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡›› አለቻት አሉ፡፡ Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 4:32 PM Yekidusan AMLAK Yitebkat enji lela min yibalal? Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 4:38 PM ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡›› አለቻት አሉ፡፡ Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 4:48 PM Thanks a lot for sharing this and I appreciate our fathers. We all know what intentional harassment to the Christians and the church is happening in our area as well. We are expecting our fathers to be courageous enough and lead Christians so as to protect our church from any type of abuse. Betekedesew Sefra Yetefate erkuset Kumo sytau anbabew Yastewel Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 4:51 PM Min Yishalal? Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 5:01 PM እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ የምንኩስና ግብር ምን ነበር ምሥጢሩ የክርስትና ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ መቃብሩን ክፈቱና አበው ይመስክሩ፡፡ እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና ጀግና ሰው አማረኝ ጠላት አሳፋሪ ንጽህት ድንግል ብሎ እምነቱን መስካሪ፡፡ ነብያት በመጋዝ የተሰነጠቁት ሐዋርያት ቁልቁል የተዘቀዘቁት ሰማዕታት በእሳት የተለበለቡት ቅዱሳን በገዳም ደርቀው የተገኙት ምሥጢሩ ምን ነበር? አበው ይናገሩት፡፡ ይናገር ዝቋላ ግሸን ላሊበላ የቅዱሳንን ዐፅም ለምን እንዳልበላ፡፡ ዋልድባ ይናገር ዜጋመልም ሳይቀር እንባቸው መፍሰሱ ለምን እንደነበር፡፡ ነበር ወይ ፈልገው ሹመት ሽልማት? ወይስ ሀብት ንብረት የተሟላ ቤት? ወይስ አምሯቸው ነው ፈልገው መሞት? እናንተ ገዳማት ምሥጢሩን አውሩት፡፡ ጐበዝ ሰው አማረኝ በእምነቱ የፀና ምግባር ሃይማኖቱ በእጅጉ የቀና፡፡ እንጦንስ የወለደው በምግባር በእምነት ተምሮ ያደገ ከተክለሃይማኖት፡፡ የጊዮርጊስ ወገን የት ነው የማገኘው? በመሀል ከተማ በአራዳ ውስጥ ነው? ወይስ በዝቋላ በደብረ ሊባኖስ በደብረ ዳሞ ነው? ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ሰው አማረው የሃይማኖት ጀግና የትነው የማገኘው? ልግባ ወይ ዋልድባ ጫካ ካለበት ማኅበረ ሥላሴ ከቅዱሳን ቤት? አክሱም ግሸን ማርያም ከቃል ኪዳን ቦታ ይገኛል ወይ ጀግና ጠላት የሚረታ? ፈሪሐ እግዚአብሔር በልቡ ያደረ ቤተ ክርስቲያንን ያልተደፋፈረ፡፡ የት ነው የማገኘው ለሃይማኖቱ ሟች ለተዋሕዶ እምነት ጠበቃ ተሟጋች፡፡ የወገን መመኪያ የከሀዲ መቅሰፍት ማነው እሱ ጀግና ተኝቶ እንደሆነ ይነሣ ቀስቅሱት፡፡ እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ የምንኩስና ግብ ምን ነበር ምሥጢሩ? የክርስቲያን ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ? መቃብሩን ክፈቱት አበው ይመስክሩ፡፡ ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ጀግና አማረው በእምነቱ የፀና የትነው የማገኘው? ብቅ ይበል እንየው እሱ ማነው ጀግና? በጐችን ከተኩላ ነቅቶ የሚጠብቅ መከራ ቢከበው ከቶ የማይሰቀቅ የሃይማኖት ጀግና ቆራጥ ሰው ገበሬ እንደዚያ እንደ ጥንቱ ይገኛል ወይ ዛሬ? የወገን የዘመድ ጥቅም ያላወረው የመናፍቆች እጅ ኪሱን ያልዳበሰው የዓለም አሸክላ ልቡን ያልማረከው የክርስቶስ ወዳጅ እሱ ጀግና ማነው? ምሥጢርን ከምሥጢሩ አንድ አድርጐ ቀምሮ ወልድ ዋሕድ ብሎ ሃይማኖት መስክሮ እንጦንስን መቃርስን በልቡ ያኖረ ከአትናቴዎስ ከቄርሎስ ጥበብ የተማረ፡፡ ድንግል እመቤቴ ብሎ የሚመሰክር መሆኗን የሚያምን ማኅደረ እግዚአብሔር ቋቅ እንትፍ ብሎ የጠላ ክህደትን ትንታግ ምላስም ጭንግፍግፉን ልሳነ ጤዛ መናፍቅን ወልደ አርዮስ ዲቃላውን፡፡ በሰይፈ ሥላሴ የሚቀላ ጀግና ማነው ዝቅ ይበላ፡፡ ነበር ወይ ያን ጊዜ ለሹመት መጓጓት እስኪ ጎርጎርዮሰ ይምጣና ጠይቁት ፍቅርንም ይጠየቅ አባ ሕርያቆስ ምሥጢርን ጠባቂ ወይም አባ መቃርስ፡፡ የክርስቶስ ባርያ የአጋንንት መቅሰፍት ወንጌል አስተማሪ የሃይማኖት አባት ይህንን ጉድ እንዲያይ ይምጣ ተክለሃይማኖት የጸሎት ገበሬ ገብረ መንፈስ ቅዱስንም ይነሣ ቀስቅሱት ይነሣ ጊዮርጊስ ይመስክር ምሥጢር የሃይማኖት ፍቅር ምን እንደነበር፡፡ ከእናቶቻችንም አሉ ለፍጥረት ያዘኑ ዲያብሎስ እንዲማር ጌታን የለመኑ፡፡ ስንቱን ልዘርዝረው የአባቶችን ሙያ መር ብለው የወጡት ከሥጋ ገበያ ጾም ጸሎት ነበረ የሃይማኖት ጋሻ መልከስከስ ምንድነው እንደ አበደ ውሻ፡፡ እንደ መስኖ ውሃ ከነዱት መነዳት ዓላማው ምንድነው የዘመኑ ወጣት፡፡ እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና ዐይኔን ሰው አማረው ጀግና ሰው ገበሬ ሃይማኖት መስካሪ እንደ ጥንቱ ዛሬ፡፡ ምንጭ፡- መለከት 1ኛ ዓመት ቁጥር 6 Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 5:11 PM how body this is!!! is this all happening in my country? we are too critics!! for the Western wellegs case, revenging persons after 100 years for attacks done by some others from the group they are is irrational!! Naftegna is group of persons that were before 50 years ago, no people or nations should be considered as naftegna!! Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 5:12 PM Thank you. I think all Ethiopian people know about the situation. It is not new information for us. Our father mentioned only five percent of the problem. Most of our church leader are working for goverment and they dont belive by God. Their main purpuses are to destroy our church, strength, unity. One years ago when Hilemariam came to the prime minister. One of weyana leader Shibat told for ESAT news. The Weyana dream is to destroy Ethiopian orthodox church and Amhara. They have been working the past 22 years but God is with us so still we are alive. The solution is to pray to God and he will give us answer soon. God bless Ethiopia. Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 5:16 PM ‹እነ ደጃዝማች እገሌ፣ እነ ፊታውራሪ እገሌ፣ እነ ራስ እገሌ እጅ አንሰጥም ብለው እየተጋደሉ ዐለፉ፡፡ ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡››Well said D.Dani Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 5:20 PM Let God be with our fathers! Dani thanks Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 5:28 PM Mechachal? Manen newe yemtechelew bete christianachene. Awo, enesu altesasatum. Yemelut, seytan ena serwitun chelachu nuru newe. Yeman bete endehon erestewal, betachene ye kirstos agerache ye egizabiher habet hager nat. Eshi, Egna enechlalen, aganentun, menafekun, sedomawiyanen. Esu amalk gene ayechelem Ferdum kerbe newe. Wow to you! Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 6:03 PM ስለቤተክርቲያናችን ከዚህ የበለጠ ልንጮህ ይገባል Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 6:06 PM Yetewededachehu Wendimoche we all know about the situation but no one is taking any initiative at least by exposing the harassment and the killings .let us work together to help this poor fathers who sacrifice a lot in every corner of the country to protect the church,just think the one who do this harassment was our followers every blog, magazine and mass media will talk about it .the harassment started before 22 years now it reaches at peak level. it is done now by using the government hands so that we should stand together to protect our church In my opinion our churches main treat comes from Neo- protestants who controlled the government higher position in Southern Region ,Oromia Region , Addis Ababa , pertialy Amahara region and mainly the Fedraral Key poations Orthodoxians Wake up. Reply Amrach Gebre sellassieOctober 17, 2013 at 6:07 PM Nበጣልያን ጊዜ ነው አሉ፡፡ ጎንደር ላይ ጣልያን በድማሚት አንዱን ተራራ ያናውጠዋል፡፡ ተራራው ‹እድም› እያለ ይፈርሳል፡፡ አንዲት የከብት እረኛ ልጅ ፈርታ ወደ እናቷ ሄደችና ‹እማዬ ኧረ ጣልያን ተራራውን እያፈረሰው ነው›› አለቻት፡፡ እናቷም ‹‹እነ ደጃዝማች እገሌ፣ እነ ፊታውራሪ እገሌ፣ እነ ራስ እገሌ እጅ አንሰጥም ብለው እየተጋደሉ ዐለፉ፡፡ ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡›› አለቻት አሉ፡፡ Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 6:33 PM Dani ejig yemiasfera zemen!!!! Elohe elohe lama sebktannnnnnnnnnni Reply WELETE MARYAMOctober 17, 2013 at 7:17 PM EGZIABHER KEGNA NEW TENKREN LEHAYMANOTACHN KOMEN BETEKRSTIYANN ENTEBK DNGL MARYAM TTEBKEN Reply Ethiopia HagereOctober 17, 2013 at 7:26 PM ዲያቆን ዳንኤል ለመረጃው እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡አባቶቻችንን አምላክ ያበርታልን ዕድሜ ይስጥልን እጅ አንሰጥም የሚሉትን ያብዛልን እኛም ተራራ ከመሆን ይሰውረን አሜን Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 8:00 PM የኢትዮጵያ አምላክ እግዚአብሔር በሀይማኖታችንና በሀገራች ፊቱን አያዞርም የመቤታችን አማላጅነትም አይለይም Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 8:03 PM የኢትዮጵያ አምላክ እግዚአብሔር በሀይማኖታችንና በሀገራች ፊቱን አያዞርም የመቤታችን አማላጅነትም አይለይም Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 8:04 PM የኢትዮጵያ አምላክ እግዚአብሔር በሀይማኖታችንና በሀገራች ፊቱን አያዞርም የመቤታችን አማላጅነትም አይለይም Reply masreshaOctober 17, 2013 at 8:27 PM አባቶቻችን ጳጳሳት እግዚአብሔር ይህንን ፍርሃት የሌለበት አገላለጻችሁ ይበል የሚያሰኝ የእውነተኛ እረኛ ድምጽ ነው እና በአንድነት ሆናችሁ ቤተክርስቲያንን /ሕዝቡን / አድኑ፡፡ እንከተላችኋለን እናንተ ግን በእውነት በርቱ እግዚአብሔር የክፉን ልብ ይመልስ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይታደግ ፡፡ ተመስገን በዋናው የሲኖዶስ ስብሰባስ ምን እንሰማ እናይ ይሆን? ለቤተክርስቲያን የሚበጅ ነገር እንድንሰማ ድንግል በቃል ኪዳኗ ትርዳን አሜን፡፡ Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 8:28 PM EGZIABHER YIMELKETEN ENJI LELAMA MIN YIBALAL? Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 8:31 PM EGZIABHER YITEBIKEN ENJI LELAMA MIN YIBALAL? Reply asbet dnglOctober 17, 2013 at 8:57 PM ዳኔ: እግዜአብሔር እየሰማን አይመስልህም ? Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 9:13 PM እውን ጳጳሳቱ ሊመነኩሱልን ይሆን፧ ቢመሽም አልነጋም። Reply DessiOctober 17, 2013 at 9:35 PM Geta hoy temelketen. Reply Semissei HabibOctober 17, 2013 at 10:04 PM actually the meeting has been much more hostile than the above. Daniel might be trying a bit moderate. Reply AnonymousOctober 17, 2013 at 10:41 PM The problem initiated when Ethiopia is led by protestant PM. As can be seen most EPRDF leaders are protestant, speacially when you go Zone and Wereda level. They are killers of history and anti-orthodox church Reply AnonymousOctober 18, 2013 at 2:29 AM Thanks danail God bless Ethiopia Reply Alemnew S. AsreseOctober 18, 2013 at 2:32 AM ‹‹ታሪክ ክፉም ሆነ በጎ እንደ ታሪክነቱ መተረክ አለበት፤ አቅራቢው ወንድማችን በ4ኛው መክዘ ክርስትና ገባ ያልከው ተሳስተሃል፡፡ ለመሆኑ ይህንን ለማለት ‹ላይሰንስ አለህ?› አባቱን የሚኮንን ልጅ ምን ያደርጋል? ነገሥታቱን ወቀሳችሁ፣ ቤተ ክርስቲያንን ነቀፋችሁ፤ ለመሆኑ ከማን ነው ይህቺን ሀገር የተረከባችሁት? ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የገባው ጌታ ባረገ ዓመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 8 ላይ አለ፡፡ ይህንን ዛሬ ‹ግራጁዌት አድርገው›፤ ልዑካኑ ስትመጡ ስለምትናገሩት ነገር ዕወቁ፤›› ብጹዕ አቡነ ማርቆስ Reply kassa mengistuOctober 18, 2013 at 5:28 AM lets stand together! my heart is broken!!! Reply SelamOctober 18, 2013 at 7:09 AM The silence should be broken properly. The EPDRF is aiming to destructing the church from the beginning. There should not be compromise on the church issue. Thank you fathers you have expressed our heart. We will follow you if you are leading us. አባቱን የሚኮንን ልጅ ምን ያደርጋል? ነገሥታቱን ወቀሳችሁ፣ ቤተ ክርስቲያንን ነቀፋችሁ፤ ለመሆኑ ከማን ነው ይህቺን ሀገር የተረከባችሁት? Best Quote from Bishop Markos of Debre Markos. Reply Load more... Older Post Home Subscribe to: Post Comments (Atom) ‹የዳንኤል ዕይታዎች› ሦስተኛ ዓመት አከባበር (ፎቶ) መጽሐፈ ጦቢት (አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ) መጽሐፈ ጦቢት (አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ) ሰው በመከራ ውስጥ እንኳን ሆኖ እግዚአብሔርን ማገልገልና ማመስገን እንደሚችል የሚያስረዳ መጽሐፍ (በዐሥራት ከበደ) አዲስ መሐፍ በገበያ ላይ አዲስ መሐፍ በገበያ ላይ ውዳሴ መስቀል ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ስለ መስቀል የደረሰው ልዩ ድርሰት በአንድ ሳምንት ያለቀ መጽሐፍ ሦስተኛ እትም በአንድ ሳምንት ያለቀ መጽሐፍ ሦስተኛ እትም ወደ አግዮስ መደብር ከመጡ በቅናሽ ይገዛሉ አዲስ የመጻሕፍት መደብር ተከፈተ አዲስ የመጻሕፍት መደብር ተከፈተ አዲስ አበባ፣ ለም ሆቴል አካባቢ፣ ማትያስ ሕንጻ ሥር፤ ትንቢተ ዳንኤል መጽሐፍ በድጋሚ ትንቢተ ዳንኤል መጽሐፍ በድጋሚ በብዙዎቻችሁ ጥያቄ መሠረት ትንቢተ ዳንኤል መጽሐፍ በድጋሚ ታትሞ ቀርቧል፡፡ one year aniversary of Daniel kibrets views ባለፉት ጊዜያት በብዙ አንባቢያን የተነበቡ አሳዛኙ ዜና click here for pdf እየሰማሁት ያለሁትን ነገር ለማመን ረዥም ሰዓት ፈጅቶብኛል፡፡ ቆይቼ ደግሞ ምናለ ውሸት በሆነ እላለሁ፡፡ አቶ መለስ ዜናዊን በዚህ ሁኔታ ማጣት አልነበረብንም፡፡ እንደ ሰው የተሳሳቷቸውን... ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ዛሬ ሌሊት ዐረፉ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ዐርፈዋል፡፡ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር ብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናትና ምእመናን ይህ ነገር በቤተ ክርስቲያኒ... የተማርንበትም የተማረርንበትም ሰሞን (ፎቶው የቢቢሲ ነው) click here for pdf የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት ከተረዳበት ሰዓት ጀምሮ ሀገራችን አዲስ መልክ ይዛለች፡፡ ያለፉት ቀናት ስለራሳችን የተማርንባቸው፤ በራሳች... በአራት ኪሎ click here for pdf ሰሞኑን በከተማችን በአዲስ አበባ ‹ነቢዩ ኤልያስ መጥቷል፣ የዓለምም ፍጻሜ ቀርቧል› የሚሉ አካላት ተነሥተዋል፡፡ እነርሱ እንደሚሉትም ነቢዩ ኤልያስ መጥቶ አዲስ አበባ ይገኛል፡፡ ቤ... የሚያሸንፍ ፍቅር አንድ ሰርግ ውስጥ አንድ ሽማግሌ ሙሽሮቹን ሊመርቁ ቆሙና « አጣልቶ የሚያፋቅር፣ አጋጭቶ የሚያጣብቅ ፍቅር ይስጣችሁ » ብለው ሲመርቁ ሰማሁ፡፡ እስካሁን ብዙ ሠርግ ተገኝቼ ምርቃት ሰምቻለ... ከ2000 ዓመት በኋላ እንደ አዲስ እንመዘገባለን፣ እንደ አዲስም እንታወቃለን click here for pdf ሰሞኑን የፌድራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሃይማኖት ተቋማትን ለመመዝገብ የወጣ ረቂቅ መመሪያ › የሚል ወረቀት አስተያየት ይሰጥበት ዘንድ ለእምነት ተቋማት አሠራጭቷል፡፡ ይህ መመርያ የያዛ... ሰው በቁሙ ሐውልት ለምን ያሠራል? በዓለም ላይ የሕዝቦቻቸውን ድምፅ የማይሰሙ እና ራሳቸው ፈላጭ ቆራጭ የሆኑ መሪዎች ባሉባቸው ሀገሮች አንድ የተለመደ ክፉ ተግባር አለ፡፡ መሪዎቹ በቁማቸው ሐውልቶቻቸውን ያሠራሉ፡፡ መንገዱን፣ ሕንፃውን፣ ስታዲዮሙን፣ ት\ቤቱን... ወላጆች፡- ሁለት ጉዳዮች አሉኝ click here for pdf አሁን ያለንበት ወቅት አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ልጆቻችን ቤት ውስጥ መዋል የጀመሩበት፣ ወይም የክረምት መክረሚያ ነገሮችን ማከናወን የጀመሩበት ጊዜ ነው፡፡ በበጋ ከነበ... አማርኛ ከሠላሳ ዓመት በኋላ click here for pdf የዛሬ ሠላሳ ዓመት በ2035 ዓም በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች መካከል የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ውድድር ይደረጋል፡፡ በውድድሩም ከዚህ በታች የማቀርብላችሁ ወግ ‹እኔና ትምህር... ቤተ ክህነትና ቤተ መንግሥት click here for pdf ብዙ ጊዜ መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው ሲባል፤ ለዚህም ሕግ ሲጠቀስ እሰማለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ግን የሚናገረው ከዚህ በተቃራኒው ነው፡፡ ቤተ መንግሥትና ቤተ ክህ... Blog Archive ▼ 2013 (71) ▼ October (4) አንድ ከሰዓት በመንበረ ፓትርያርክ ዋልያው ንሥሩን ጋለበው የሁለት አይጦች ወግ አርጤምሳውያን ► September (5) ► August (9) ► July (6) ► June (6) ► May (7) ► April (7) ► March (9) ► February (8) ► January (10) ► 2012 (119) ► 2011 (148) ► 2010 (123) Me My Photo ዳንኤል ክብረት started on march 22, 2010 email: dkibret@gmail mobile 251911474503 View my complete profile ቢያዩዋቸው ይጠቀማሉ Bereket Mamo Mekele Debre Amin Abune Teklehaimanot Church Public Hospital and Medical College ሸገር ሬድዮ አኰቴት ዘተዋሕዶ መንፈሳዊ የቴሌቪዥን መርሐ ግብር አግዮስ ኅትመት የመልአኩ እዘዘው ጦማር የብስራት እይታ የኤፍሬም እሸቴ ጦማር ሰሞነኛ ጉዳዮች አምፖልና ኩራዝ click here for pdf ኩራዝ ከጓሮ ማድቤት ተወሽቃ ትኖር ነበር፡፡ ለብዙ ዘመናት፡፡ ድንገት ሳሎን የምግብ ጠረጲዛ ላይ ታየች፡፡ ይህ ነገር ኮርኒስ ላይ የተንጠለጠለችውን አምፖል በእጅጉ አስገረማት፡፡ ‹‹ኩ... ዋልያው ንሥሩን ጋለበው click here for pdf ‹ይህቺ ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር የሚጠብቅና የሚታደግ አንዳች ኃይል አለ› የሚባለውን ነገር እንድናምን የሚያደርጉ ብዙ አጋጣሚዎች አሉ፡፡ ሕዝቧ ብትን፣ ቅዝቅዝ፣ ድብዝዝ ሲል ከየት... አናብስት click here for pdf ቀነኒሳን አንበሳ አሉት፡፡ ኃይሌንም አንበሳ አሉት፡፡ እንደምን ነው ቢሉ፡፡ አንድም አንበሳ ሲተኛ የሞተ፤ የደከመ፣ የታመመ ይመስላል፡፡ እንስሳት እየመጡ ይጎበኙታል፡፡ ያዩታል፤ አንዳ... የሁለት አይጦች ወግ click here for pdf ‹ዛሬ በናትሽ ዳጎስ ያለ ሰነድ ወይም መጽሐፍ ወይም ዶሴ መብላት አማረኝ›› አለች አንዲት ነጭ አይጥ ለጓደኛዋ፡፡ ‹‹ለምን አንዱ የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት አልወስድሽም›› አለቻት ጥቁሯ ... አርጤምሳውያን click here for pdf ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዛሬዋ ቱርክ ኢያዞሎክ፣ በጥንታዊቷ የኤፌሶን ከተማ ተገኝቶ ነበር፡፡ በዚህች ከተማ እጅግ የታወቀች፣ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች አማንያን የሚጎርፉላት፣ ምስሏን የሚ... አንድ ከሰዓት በመንበረ ፓትርያርክ click here for pdf የመንበረ ፓትርያርክ 32ኛው ጉባኤ የረቡዕ ዕለት ከሰዓት ውሎ ካለፉት የተለየ ነበር፡፡ ዋና አጀንዳው ‹መቻቻልን› የተመለከተ ሲሆን አቅራቢዎቹም ከፌዴራል ጉዳዮች የተወከሉ አካላት መሆ... ኑሮ በካንጋሮ ምድር (ክፍል ፫) click here for pdf እዚያው ፉትስክሬይ ቁጭ ብለን ወግ በመሰለቅ ላይ ነን፡፡ ባለፈው ወዳጄ ስለ ‹‹ኢምፖርት›› አንሥቶ ነበር ያቆመው፡፡ እስኪ ይቀጥል፡፡ ‹‹ምንድን ነው ኢምፖርት የሚያደርጉት ኢትዮጵ... Amharic Font If you are not able to read this page, please click here. join us on google + Awesome Inc. template. Template images by wingmar. Powered by Blogger.
Posted on: Fri, 18 Oct 2013 06:13:09 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015