#Ethiopia: Controversy over Dawit Kebedes claim Chinas ZTE telecom - TopicsExpress



          

#Ethiopia: Controversy over Dawit Kebedes claim Chinas ZTE telecom hacked AwrambaTimes website j.mp/1sZ0h5a አውራምባ ታይምስ ድረገፅ በዜድቲኢ ኩባንያ ተስተጓጉሏል መባሉ አወዛገበ በ ፋኑኤል ክንፉ “የድረ ገፄ ሚስጥር ቁልፍ በዜድቲኢ ተሰብሯል” አቶ ዳዊት ከበደ የአውራምባ ታይምስ ድረገፅ ባለቤት “መልካም ስማችንን ለማጥፋት የተቀነባበረ ውንጀላ ነው” ወ/ሮ የምስራች ብርሃኑ የዜድቲኢ ሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰር አውራምባ ታይምስ ድረገፅ ከግብር አከፋፈል ጋር በተያያዘ በዜድቲኢ ኩባንያ ላይ ዜና በማሰራጨቴ የኩባንያዬ የድረ ገፅ ሚስጥር ቁልፍ በዜድቲኢ ተሰበረብኝ፣ ችግርም ፈጠረብኝ ብሏል። ዜድቲኢ በበኩሉ የኩባንያውን መልካም ስም ለማጥፋት የተቀነባበረ ውንጀላ ነው ሲል ክሱን አስተባብሏል። የአውራምባ ታይምስ ድረ ገጽ ባለቤትና መስራች አቶ ዳዊት ከበደ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት፤ “ዜድቲኢ ለገቢዎችና ጉምሩክ መክፈል ስላለበት የግብር መጠን ጠቅሼ ዜና ማሰራጨቴን ተከትሎ ኩባንያው በዚህ በመበሳጨት የድርጅቴን ድረ ገጽ በተገቢው ሁኔታ እንዳይሰራ በማድረግ ከአንድ ሳምንት በላይ ከስራ ውጪ እንድሆን ተገድጃለሁ። አንባቢዎቼም ተገቢውን የመረጃ አቅርቦት እንዳያገኙ ሆነዋል” ብለዋል። “አሁን ለሰነዘሩት ውንጀላ ምን ማስረጃ አልዎት” ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ “የመረጃ ቋት የተከራየሁት አሜሪካ ሀገር ካሊፎርኒያ ከተማ ከሚገኘው ስካላ ከተባለ የመረጃ ቋት ቦታ አከራይ ኩባንያ ነው። ይህ ኩባንያ የሰጠኝ መረጃ እንደሚያሳየው ሰበራው የተደረገበት መነሻ ቦታ “55,Hi-tech Road South, ShenZehen, P.R.China” ሲሆን የኮምፒውተሩ አድራሻ “IP address j.mp/1sZ0h5a
Posted on: Thu, 14 Aug 2014 15:32:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015