የበጎ ዋጋው ከ 6 ወራት በፊት የ 55 ዓመቱ፣ - TopicsExpress



          

የበጎ ዋጋው ከ 6 ወራት በፊት የ 55 ዓመቱ፣ የካንሳስ ነዋሪ ሃሪስ ጎዳና ተዳዳሪ ነበር። በአንድ የካንሳስ አውራ ጎዳና ላይ ሲቀመጥ ለነፍሱ ያለ ሰው ያለው ፍራንክ ጣልጣል እያደረገለት ለበርካታ ዓመታት ኖሯል። አንድ ቀን አንዲት ዳርሊንግ የተባለች የካንሳስ ነዋሪ (ስሟ እንዴት ደስ ይላል)፣ ቢሊ ባለበት ቦታ ስታልፍ ፣ ቦርሳዋ ውስጥ ያለውን ዝርዝር ሳንቲም በሙሉ ዘርግፋለት አለፈች። እሱም አመስግኗት ፣ ሳንቲሙን ሲቆጥር መካከል ላይውድ የአልማዝ የጋብቻ ቀለበት ያያል። ግራ ገብቶት ቀና ሲል እሷ የለችም። አንድ ሱቅ ጎራ ብሎ ስንት እንደሚያወጣ ሲያጣራ 4ሺ ዶላር የሚያወጣ ቀለበት እንደሆነ ይነገረዋል። አሁን ሃሪስ አሰበበት፣ እንደሱ ላለ ጎዳና ተዳዳሪ 4ሺ ዶላር ብዙ ገንዘብ ነው። ቢሆንም ግን የጋብቻ ቀለበት መሆኑ ልቡን ነካው - ኪሱ አስቀምጦ ልመናውን እዚያው ቦታ ቀጠለ። በማግስቱ ዳርሊንግ መጣችና ትናንት ሳንቲም ስትሰጠው ቀለበት አብራ ሰጥታው እንደሆነ በማስተዛዘን ጠየቀችው። እሱም አላሳፈራትም - “ቀና ስል እኮ የለሽም ፣ ይኸው አስቀምጫዋለሁ” አለና መለሰላት። ዳርሊንግ አላመነችም - በጣም አመሰገነችው - ተመልሳ እንደምትመጣም ነግራው ወደ ባሏ ሮጠች። ይህ ከሆነ 6 ወር ሆነው። ታዲያ ዳርሊንግ እና ባለቤቷ ቢል ፣ ቢያንስ 1ሺ ዶላር ያህል ከሰዎች ሰብሰበው ለበጎ ሥራው ውለታ ሊሰጡት ፈለጉና ያረገውን አውርተው እርዳታ ጠየቁ። በሶስት ወር ጊዜ ግን 1ሺ ሳይሆን 190ሺ ዶላር ተሰበሰበ። ሃሪስ ተደሰተ - አዲስ መኪናም ገዛ፣ ታሪኩን የሰሙ ሁሉ አይዞህ አሉት። ከነ ዳርሊንግ ጋርም ቤተስብ ሆነ። የከተማው ቴሌቪዥንም ቃለመጠይቅ አደረገለት። በዚህ ጊዜ ደግሞ የት እንደገባ ጠፍቶባቸው የነበሩ ቤተሰቦቹ ፈልገው አገኙት። ከቤተሰቡም ተቀላቀለ። አቅሙ የሚችለውን እየሰራ፣ በመኪናውእየተንደላቀቀ፣ ከቤተሰቦቹ ተቀላቅሎ ኑሮውን ጀመረ። አሁን ጥሩ ፍቅረኛ እየፈለገ ነው። በስድስት ወር ውስጥ የሃሪ ታሪክ ተቀየረ። ቱዴይ ጋዜጣ ሴፕቴምበር 1 ቀን አወራው - ድንቅ መጽሄት ለናንተ ወደ አማርኛ ተረጎመላችሁ። ስንዴ ከዘራህ ስንዴ፣ እንክርዳድም ከዘራህ እንክርዳድ ታጭዳለህ። በተለይም ከዚህ አዲስ ዓመታችን ጀምሮ ስንዴ ዘሪዎች እንሁን።
Posted on: Mon, 02 Sep 2013 22:08:44 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015