ወይ #አዲስ_ጉዳዮች በቃ በለውጥ ፣ - TopicsExpress



          

ወይ #አዲስ_ጉዳዮች በቃ በለውጥ ፣ በአዲስ መልክ እንመጣለን እያሉ የአንድ ገጽ ማስታወቂያ ሲሰሩ ማንን ምሳሌ ሊያደርጉ ነው The New Yorker ወይስ The Economist አይይ በቃ እንደ Time ሊሆኑ ነው ምናምን እያልኩ መባተሌ … ሊፎግሩ ነው ግን? አዲስ መልክ የሚሉት? ይልቅ ሌሎችንም ጸሐፊዎችንም ጥሩ እየከፈሉ ቢያመጡ ጥሩ ነው ፤ ደግሞም ድርግም አድርጎ ምንም ሳያጣቅሱ ነገር በሶስት ይከፈላል ፣ አምስት ዓይነት ምልከታ አለው ምናምን ምናምን የሚለውን ፊቸር ጹሑፋቸውንም አዲስ መልክ ቢሰጡት ሸጋ ነበረ…መጽሔት ደግሞ ፊቸር ከሌለው ምን እርባና አለው?
Posted on: Sat, 27 Jul 2013 11:02:04 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015